በቅርቡ ይመጣል
Meskerem (መስከረም)
የአዋጅ ነጋሪ ቃል በበረሃ አየለ
Lyrics:
የአዋጅ ነጋሪ ቃል በበረሃ አየለ
የ እግዚአብሔርን መንገድ አስተካክሉ እያለ
ምስክርነቱን ዮሐንስ ሲያስረዳን
ልባችሁ ለጌታ መልካም መንገድ ይሁን!
❤
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አውደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም
❤
ተራራው ዝቅ ይበል ጠማማውም ይቅና
ካልተስተካከለ መንገድ የለምና
የ እግዚአብሔርን መንግስት እንመስርት ሁላችን
ማረፊያ እንዲሆነን ለመጪው ሃብታችን
❤
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አውደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም
❤
ክፋትና ተንኮል ከልባችን ይጥፋ
ጽድቅና ርህራሄ በኛ ላይ ይስፋፋ
ሥጋና ደምህን በክብር አግኝተናል
ህይወት እንዲሆነን አምላክ ተማጽነናል
❤
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አውደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም
❤
ሁለት ልብሶች ያሉት ከማብዛት ልብሱን
ለሌለው ያድለው ሁለተኛውን
ከበደላችንም አንጻን አደራህን
በክፉ እንዳንጠፋ እኛ ባህሮችህ
❤
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አውደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም