ከ1938 እስከ 1973 የቀድሞውን የእንጦጦ መንበረ ሥላሴ የቦታ ይዞታን እና የቀድሞውን ህንፃ ቤት ክርስቲያን በሁለት ዓመት ውስጥ ገንብተው በማጠናቀቅ የሰጡት አባ ኃይለሣላሴ መገኖ ናቸው። ይህ የቀድሞ ህንፃ በዕድሜው ብዛት እና ን1953 ዓ.ም በኢትዮጵያ በደረሰው የመሬት መናወጽ ምክንያት ክፎኛ በመጎዳቱ እና አደጋ የሚያደርስ መሆኑን በምህንድስና ባላሙያዎች በ1976ዓ.ም ትረጋግጧል
እንግዲህ በዚህ ጊዜ ነው ከአካባቢው ነዋሪ ምዕመናን የተመረጡ ሰዎችን ያቀፈ እና በወቅቱየቤት ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ መምህር ወይም አባ ወልደ ገብርኤል ወርቅዬን ያካተተ 25 አባላት ያሉት የእንጦጦ መንበረ ሥላሴ ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ በሚል ስያሜ ተቋቋመ። የህንፃው ስራው ኮሚቴው ታሪክ ላለመሻር በሥላሴ ፈቃድ አባ ኃይለ ሥላሴ መገኖ የበፊቱን ቤት ክርስቲያን መሰረት ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ያስኖሩበትን ዕለት ኅዳር 6 ቀንን በማስታወስ ኅዳር 7 ቀን 1981ዓም የመሰረት ቆፋሮ ሥራ ተጀመረ። የህንፃውን ስራ በመሃንድስነትና በአማካሪነት እንዲሁም የህንፃወን ፕላን እንዲያሻሽሉና ቅርጽና ጌጡን እያሳመሩ ከቆዩ በኃላ የህንፃውን ምርቃት ስራዓት ሳያዩ በ1990 ዓም በሞት የተለዩት ጣሊያናዊው ኢንጅነር ቬንዲቶ ኦሜዲዩ ናቸው።
የህንፃው ስራ አልቅ እነሆ ኅዳር 7 ቀን 1991 ዓም ይህ አዲስ ቤተክርስቲያን ለመመረቅ በቅቷል።የቤተ ክርስቲያኑ ይዞታ እና የቀድሞውን ቤተ ክርስቲያን በማሰራት ለህዝበ ክርስቲያን ያበረከቱት አባ ኃይለ ሥላሴ መገኖ ኅዳር 15 ቀን 1955 ዓም አርፈዋል። አጽማቸውም በአዲሱ ቤተክርስቲያን ምድር ቤት ወስጥ አርፏል።
