የመንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት\ቤት የተመሰረተው በ1954ዓም ሲሆን ዉሉደ ብርሃን የሚለውን ስያሜ የሰጡት በቀቅቱ የነበሩት የማህበሩ አባላት አንድ ሰው ናቸው።
ሰንበት ት\ቤቱ ሲመሰረት 13 ሴቶችና 17 ወንድሞች ባጠቃላይ 30 አባላት ነበሩ። እነዙ ወጣቶች በወቅቱ የአካባቢው ህብረተሰብ ቃለ እግዚአብሔር እንዲማር የተለያዩ መንፈሳዊ ተውኔቶችን እያዘጋጁ በየባዕላቱ አውደ ምህረት ላይ ያቀርቡ የነበረ ሲሆን በዋናነት ደግሞ ወጣቶች በሃይማኖት እንዲጎለብቱ በሥነ ምግባር እንዲታነጹና በወቅቱ ብቅ ብቅ ማለት በጀመረው በመናፍቃን ትምህርት እንዳይታለሉ ከፍተኛ አገለግሎት ተፈፅም ነበረ።
ለአብነት ያህል በራሳቸው ወጣቶች የተደረሰው የተዘጋጀና የተተወነ “ ቢያድግልኝ” የተሰኘው ተውኔት በጠቅላይ ቤትክህነት አዳራሽ ተጋብዘው ለህዝብ ያቀረቡትን ማቅረብ ይቻላል። አሁን ፈርሶ የቤተ ክርስቲያኑ ጽ\ቤት የተሰራነት ስፍራ ላይ የነበረውን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ራሳቸው እንጨት ተሸክመው ከኪሳቸው ገንዘብ አውጥተው እንዲሁም ከላይ በተጠቀሰው ተውኔት ቢያድግልኝ በተሰኘውና ከሌሎች ሰንበት ት\ቤቶች ግስር በመተባበር የስቅለትን በዓል ምክንያት በማድረግ በጠቅላይ ቤተክህነት ባዘጋጀው የሥነ ስቅለት ተውኔት ግርማዊ ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ በተገኙበት የሰንበት ት\ቤቱ 8 አባላት ተሳታፊ በመሆናቸው በተገኘው የገንዘብ ገቢ ጥቂት ቁሳቁሶችን በማሟላትና በጎ ፈቃደኞች ባለሙያዎች ትብብር በመጠየቅ እንዲሁም የተለያዩ የገንዘብ ማስገኛ መንገዶችን በመጠቀም ሊሰሩ ችለዋል።
ምንም እንኳ የየሰንበት ት\ቤቶች ጥቅም ምን እንደሆነ ያልታወቀበት ዘመን በመሆኑ ክህብረተሰቡ ትልቅ ተቃውሞ የነበራቸው ቢሆንም በከፍተኛ ጥረት ትምህርት የህብረተሰቡን አስተሳሰብ በመቀየርና አገልግሎቱ ቀጣይነት እንዲኖረው በማድረጋቸው ሰንበት ት\ቤቱ አሁን ላለበት ደረጃ እንዲደርስ አድርገውታል።
በአሁኑ ወቅት ከቀድሞ በተሻለ መልኩ ሰንበት ት\ቤቱ የብዙ ዜጋ ወጣቶች ማፍሪያ ቦታ ሆናአል።
