Advertisement Image

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

መሰረታዊ የክርስትና ትምህርቶች እና ትንታኔዎች

የመጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፎች

ምዕራፍ አንድ : የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና ትርጉም

1.1 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማለት ምን ማለት ነው?
መጽሐፍ ማለት-በአንድ ጥራዝ ውስጥ የተካተቱ (የተከማቹ) ጽሐፎች ስብስብ ማለትነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የተለያዩ ቅዱሳት መጽሐፍት በአንድ ላይ ተሰበስበው የሚገኙበት የመጽሐፍት መድብል ነው፡፡

ቅዱስ ማለት-የተለየ፣የተከበረ፣የተቀደሰ ማለት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ምድራዊያን መጽሐፍት በዘመን የሚወሰን በሰዎች የሚሻሻል ሳይሆን እንደ ዘመናት የማያልፍ፤አንባቢውን የሚቀድስ የተለየ፣የተቀደስ መጽሐፍ ነው፡፡

ጥናት-አንድን ነገር በጥልቅት መመልከት በነገሩ ላይ በቂ ግንዛቤ መያዝ እና ማስጨበት መቻል ማለት ነው፡፡

1.2 መጽሐፍ ቅዱስ የማጥናት ጥቅም
I. እግዚአብሔርን የበለጠ ለማወቅ እና ለመቀደስ
ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሰለተጻፉ ጽሑፎች የምንረዳበት ነው፡፡እግዚአብሔር አምላካችን ለፍጥረቱ በስነ ፍጥረት፤ በመጽሐፍት እና እራሱ በመገለጥ ስለእሱ እንዲውቁ አድርጓል፡፡ የስነ- መለኮት ሊቃውንት ምክንያቱን ሲያሰረዱ ፍጹም ኃያል የሆነው እግዚአብሔር በፍጡሩ ሊመረመር የማይችል በመሆኑ በመጽሐፍት እና በስነ-ፍጥረት እራሱን ለፍጡሩ ገልጧል፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔር ኃይሉ፤ ክብሩ፤ ባህሪው፤ ፈቃዱ፤ አሰራረር ወዘተ ተገልጾል፡፡ ሰለዚህ ስለመጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት እግዚአብሔርን የበለጠ ለማወቅ እና ለመቀደስ ይጠቅማል፡፡

II. ክፉን ከበጎ ለመለየት ይረዳል
የእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ነው፡፡በቃሉ ብርሃንነት ክፉን ከደጉ፤ ደጉን ከከፉ ለመለየት መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ጠቃሚ ነው፡፡”ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው::” መዝ 118፤105 እንዳለ ቅዱስ ዳዊት፡፡

“የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።” 2 ጢሞ 3፤ 17

III. ለመቀደስ
መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በቅዱሳን ሰዎች የተጻፈ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ሰለሆነ የሚያነቡትን፤ የሚሰሙትን፤ የሚያጠኑትን እና የሚጸልዩትን ይቀድሳል፡፡‹‹በእውነትህ ቀደሳቸውቃልህ እውነት ነው፡፡››ዮሐ 17፤17 (ኤፌ 5፤26)

IV. ጥበብ ስጋዊ እና ጥበብ መንፈሰዊ ለማግኘት
መጽሐፍ ቅዱስ የጥበባት ሁሉ ምንጭ ነው፡፡መንፈሳዊ ጥበብ እግዚአብሔርን በመፍራት እንደሚገኝ ያስተመረናል፡፡ (ምሳ 1፤7) በተጨማሪም ስጋዊ ጥበቦች ያሰተምረናል፡፡

- የምህድስናምንጭነው (ዘፍ 6፤14-16 2ዜና 3፤3-4 1ነገ 6፤1-38 ዘጸ 36፤1-40)
- የሕክምናምንጭነው (ኩፋ 10፤7 ት.ኢሳ 38፤21 ሉቃ 10፤29-37)
- የግብርና ምንጭ ነው(ዘፍ 3፤17-23 ዘፍ 41፤25-36 ዘዳ 23፤10)
- የአስተዳደር ምንጭ ነው (ዘጸ 18፤13- 25 ዘጸ 32፤32 1ነገ 17፤28)

1.3 መጽሐፍቅዱስ ከሌሎች መጽሐፍት በምን ይለያል
ሀ. አስገኝው እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆ
መጽሐፍቅዱስ የሚናገርው ስለ ቅዱሱ እግዚአብሔር በመሆኑ ከሌሎች መጽሐፍት ይለያል፡፡ ሌሎች መጽሐፍት(አለማዊያን መጽሐፍት) የተገኙት ከስው ሲሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ከቅዱሱ እግዚአብሔር የተገኘ በመሆኑ ቅዱስ ነው፡፡ ‹‹እኔ ቅዱስ እንደሆንኩኝ እናተ ቅዱሳን ሁሉ››ዘሌ 19፤2

ለ. በእግዚአብሔር መንፈስ የተነሳሱ ቅዱስን አባቶች የጻፉት በመሆኑ
መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በቅዱሳን አበው ነው፡፡ ‹‹በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ትንቢት ከቶ በስው ፈቃድ አልመጣም እና ዳሩ ግን በአግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ፡፡›› እንዲል 2ጴጥ 1፤20-21 (ዘጸ 17፤14 ራዕ 2፤7)

ሐ. ዘመን የማይሽረው በመሆኑ
ዓለማዊያን መጽሐፍት በየጊዜው ከለውጦች ጋር በተገናዘበ መልኩ ሲለወጢ፣ ሲቀየሩ ፣ሲሻሻሉ እና ሲሻሩ ይታያል፡፡ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ በጊዜ ብዛት የሚሻር እና የሚሻሻል ሳይሆን በዘመናት የማይገደብ የህያው የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የማይሽርው ባለስልጣን በስልጣኑ የማይለውጠው ዘላለማዊ ህግ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ከላይ ከሰማይ የተሰጠ ሰማያዊ ዓላማ ያለ አምላካዊ መጽሐፍ ነው፡፡ ዓላማውም ፍጥረት ሁሉ(የስው ልጅ) መንግስተ ሰማያትን እንዲወርስ ማስቻል ነው፡፡ ሰለዚህ በዘመን የማይገደብ ዘላለማዊ መጽሐፍ ነው፡፡‹‹ ሰማይ እና ምድር ያልፋል ቃሌ ግን አያልፍም›› ማቴ 23፤35 (ት.ኢሳ 40፤8 1ኛ ጵጥ 1፤25 12፤5 ዘዳ 31፤19)

መ. የሚያነቡትን እና የሚሰሙትን ሰለሚባረክ
መጽሐፍ ቅዱስ የሚመክር፣የሚገስጽ፣ የሚያረጋጋ የሰውን ልጅ ወደ ቅድስና የሚመራ መጽሐፍ ነው፡፡ (ዘሌ 19፤21 1ጵጥ 1፤15 መዝ 118፤103-105 22፤4 ሉቃ 4፤14 7፤7 ሐዋ 13፤26)

ሠ. የሰው ልጅ ከመፈጠሩ በፊት ስለነበር ሁኔታ በእርግጠኝነት ስለሚናገር
መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ልጅ ከተፈጠረ ከአንድ ሺ (1000) ዓመታት በኃላ መጻፍ የተጀመረ ቢሆንም የሰው ልጅ ከመፈጠሩ በፊት ሰለነበረው የሥነ-ፍጥረት ስራ በእርግጠኝነት ይናገራል፡፡‹‹ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይ እና ምድር ፈጠረ፡፡›› ዘፍ 1፤1 (ዩሐ 1፤1) በሌሎች መጽሐፍት ግን ይህን በመላምት እንጂ እረገጠኝነት በተላበሰ መልኩ ማገኘት አይቻልም፡፡

ረ. ወደፊት ሰለሚመጣው በእርግጠኝነት የሚናገር በመሆኑ
መጽሐፍ ቅዱስ ሰለሚመጣው ዘመን በእርግጠኝነት የሚናግር መጽሐፍ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ የተነገሩ ትንቢቶች ሁሉ የተፈጸሙ እና እየተፈጸሙ የሚገኙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ነብዩ ኢሳይያስ ክርስቶስ በድንግልና ሰለመወለዱ ከሰባት መቶ ዓመታት በፊት የተነበየ ሲሆን የትንቢቱን ፈጻሜ በሐዲስ ኪዳን በወንጌል ተጽፎ እናገኘዋለን፡፡ ‹‹እንሆ ድንግል በድንግልና ተፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ተለዋለች…›› ት.ኢሳ 7፤14 (ሉቃ 1፣25 መዝ 77፤65 46፤5 ማቴ 24)

ቀ. ሰውን ወደ ቅድሳና የሚያደርስ በመሆኑ
በመጽሐፍ ቅዱስ የጠቀሱትን ትምህርቶች፣ ምክሮች፣ተግሳጾች አንዲሁም ትዕዛዞች የሚጠብቅ እና የሚተገብር ስው በቅድስናን መንግድ ላይ የሚጓዝ ነው፡፡ ‹‹ የዚህ መጽሐፍ ትንቢት የሚጠብቅ ብፁዕ ነው›› ራዕ 2፤7

1.4. መጽሐፍ ቅዱስ መቼ በማን ተጻፈ?
1.4.1 መጽሐፍ ቅዱስ በማን ተጻፈ?
መጽሐፍ ቅዱስን ቅዱሳን አባቶቻችን በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርተው ጻፉት፡፡ በሁሉም አባቶች(ነብያት፣ ሐዋርያት፣ አርድዕት እና ሊቃውንት) ላይ አድሮ ምስጢር የገለጸ፣ የመራ እና ያናገር የእግዚአብሔር መንፈስ ነው፡፡(ዩሐ 14፤26) ቅዱሳን ሰዎች በገዛ ፈቃዳቸው ተነስተው የጻፉት ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፈ ነው፡፡‹‹ ይህን በመጀመርያ ዕወቁ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም በገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ትንቢት ከቶ በስው ፍቃድ አልመጣምና ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ስዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ተናገሩት›› 2ኛ ጵጥ 1፤20-21 (ራዕ 1፤11 ት.ኢሳ 8፤1 ት.ኤር 36፤2 ዘጸ 34፤27)

መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው ከተለያዩ የስራ መስኮች በተጠሩ ቅዱሳን ሰዎች አማካኝነት ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎት ከተመረጡ ቅዱሳን አበው መካከል የተወሰኑትን ከምን የስራ መስክ እንደተጠሩ እንመለከት፡-

ለምሳሌ o ከእረኝነት ሙሴ /ዘጸ 3፤1/ - ከቀራጭነት ማቴዎስ /ማቴ 9፣9/ o ከነገስታት ዳዊት እና ሰሎሞን /ዜና 29፤28/ - ከካህናት ሕዝቅኤል /ት.ሕዝ 1፣3/ o ከዓሳ አጥማጅነት ጵጥሮስና ዩሐንስ… /ማቴ 4፣18-22/ - ከሕክምና ሉቃስ /ቆላ 4፤4/

1.4.2 መቼ ተጻፈ?
መጽሐፍ ቅዱስ በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ቅዱሳን አባቶች ተጽፎል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ከ 1400 ቅ/ል/ክ እስከ 100 ድ/ል/ክ ድረስ እንደተጻፈ ይታመናል፡፡ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ከ1400-400 ዓ.ዓ (ቅ/ል/ክ) በ32 በሚደርሱ ቅዱሳ አባቶች የተጻፈ ሲሆን የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት ከ45-100 ዓ.ም (ድ/ል/ክ) ከ8 በላይ ቅዱሳን አባቶች ተጽፎል፡፡እንደ ሊቃወንት ቤ/ክ አስተምሮ መሰረት በመጀመርያ የተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል መጽሐፍ ሄኖክ ሲሆን በመጨረሻ የተጻፈው ራዕይ ዮሐንስ ነው፡፡

1.5 መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈባቸው ቋንቋዎች
የብሉይ ኪዳን መጽሐፍቶች በዕብራይስጥ እና በአረማይክ ቋንቋ የተጻፉ ሲሆን የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት ደግሞ አብዛኞቹ በግሪክ ቋንቋ ተጽፈዋል፡፡ በአጠቃላይ መጽሐፍ ቅዱስ በአራት አገር ቋንቋዎች የተጽፏ፡፡ እነርሱም
- ዕብራይስጥ
- አረማይክ
- ሮማይስጥ
- ግሪክ /ፅር/ ቋንቋዎች ናቸው፡፡
አብዛኞቹ የብሉይ ኪዳን መጸሐፍት በዕብራይስጥ እና በአረማይክ ቋንቋ ተጽፍዎል፡፡ ዕብራይስጥ እና አረማይክ ቋንቋ በሲሚቲክ የቋንቋ ምድብ ውስጥ ይመደባል፡፡ አብዛኖቹ የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት በግሪክ/በጽዕር/ ቋንቋ ተጽፏል፡፡ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚነሳው የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት በተጻፉበት ወቅት የግሪክ ቋንቋ አብዛኞቹ የአለም ሀገራት የሚነገር በመሆኑ ወንጌልን ሁሉም ስው እንዲሰማው እበዛኞቹ ሰዎች በሚደምጡት/በሚናገሩት/ በግሪክ ቋንቋ እንዲጻፍ ሆኗል፡፡

1.6 የቅዱሳት መጽሐፍት ትርጉም
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ቃል የያዘ በመሆኑ ለተወሰነ ህዝብ ብቻ የተሰጠ ሳይሆን ለመላው አለም እንዲማርበት እና እንዲታረምበት፣አምልኮቱን እንዲገለጥበት፣ስለእግዚአብሔር እንዲያውቅበት ተሰጧል:: ስለዚህ ቅዱሳት መጽሐፍት ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች መተርጎም አስፈለገ:: እግዚአብሔር አምላክ በየዘመናቱ የሚጽፉና የሚተረጉሙ ሰዎችን አስነስቷል:: ኢትዮጵያ በዕብራይስጥ ተጽፎ የነበሩትን የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ወደ ግዕዝ ቋንቋ በመተርጎም ቀዳሚት አገር ናት:: በ900 ዓ.ዓ ገደማ ከቀዳማዊ ምኒሊክ ጋር የመጡት 318 የአይሁድ ሊቃውንት የግዕዝ ቋንቋን በማጥናት ተርጉመውታል:: በ284(275) ዓ.ዓ ቅ.ል.ክ(ቅድመ ልደተ ክርስቶስ) ገደማ 72 ሊቃውንት ከዕብራይስጥ ወደ ግሪክ/ጽዕር/ ቋንቋየብሉይኪዳንመጽሐፍትበበጥሊሞስዘመነ መንግስት ተረጎሙት::የብሉይ ኪዳን መጽሐፍትም ከዕብራይስጥ ወደ አርማይክቋንቋ ተተርጉሟል::