Advertisement Image

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

መሰረታዊ የክርስትና ትምህርቶች እና ትንታኔዎች

የመጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፎች

ምዕራፍ ሶስት : የመጽሐፍ ቅዱስ አከፋፈል

3.1 የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን አከፋፈል
ብሉይ ኪዳን
ኪዳን- ኪዳን ማለት በሁለት ወገኖች መካከል የሚደረግ ውል(ስምምነት) ማለት ነው:: እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ጋር ያደረገው ውል፣ስምምነት ማለታችን ነው::በዚህ መሰረት ለኪዳን ሁለት ወገኖች ያስፈልጋሉ:: ውል ሰጪና ውል ተቀባይ:: ከዚያም መኃላው(ኪዳኑ) ይኖራል:: እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ በኪዳኑ አልተለየውም:: (ዘፍ 1፤26-28)

ብሉይ - ማለት የቆየ፣የጥንት፣የበፊት፣ቀዳማዊና የድሮ ማለት ነው:: ብሉይ ኪዳን ማለት ጥንታዊ፣ቀዳማዊ ውል(ስምምነት) ማለት ነው:: ይህ ውል በሙሴ አማካኝነት እግዚአብሔር ለእስራኤላዊያን የገባውን ኪዳን የያዘ ነው:: ይህ ኪዳን ከፍጥረት ዓለም እስከ ክርስቶስ መወለድ ድረስ ያለውን ታሪክ በውስጡ የያዘ ነው:: የብሉይ ኪዳን መጽሐፍትየተጻፉት ከ1400-400ዓ.ዓ(ቅ.ል.ክ) ድረስ ባሉት 1000 ዓመታት ውስጥ ነው:: የተጻፈውም ስላሳ ሁለት(32) በሚደርሱ አባቶች ነው:: የተጻፈውም በዕብራይስጥቋንቋ ነው:: ብሉይ ኪዳንን ብሉይ ኪዳን ያሰኘው እግዚአብሔር አምላካችን ከእስራኤል ዘነፍስ ጋር ያደረገው አዲስ ውል ወይም ስምምነት(ሐዲስ ኪዳን) ሲመጣ ነው::(ኤር 31፤31 ማቴ 26፤26-29 1ኛ ቆሮንቶስ 11፤25-26)

ብሉይ ኪዳን ተሽሯል የሚለው አስተምህሮ የተሳሳተ ነው:: ብሉይ ኪዳን በሐዲስ ኪዳን መምጣት ጸንታለች፣ከብራለች::(ማቴ 5፤19-20) ጌታችን ወንጌልን ሲያስተምር ከብሉይ ኪዳን እየጠቀሰ ማስተማር ለዚህ በቂ ማሳያ ነው:: ‹‹ህግና ነቢያትን ልሽር የመጣሁ አይምሰላችሁ ልፈጽም እንጂ›› ማቴ 5፤17፡፡ በህግና በነቢያት ስለ እርሱ የተነገሩትን ለመፈጸም የወጣ መሆኑን አስተምሮናል:: ስለዚህ ብሉይ ኪዳን የሐዲስ ኪዳን ምስክር ፣ንባብ፣ትርጓሜ፣ፍጻሜ ናት:: ቅዱስ አወግስጢኖስ የተባለው የቤተ-ክርስቲያን ሊቅ ‹‹ሐዲስ ኪዳን በብሉይ ኪዳን ተሰውሯል፡፡ ብሉይ ኪዳን በሐዲስ ኪዳን ተገልጧል›› በማለት ተናግረዋል::

የሁለቱ ኪዳናት አንድነት
ሁለቱም ኪዳናት የሚገለጡት(የሚስተማሩት) ስለ እግዚአብሔር ነው::በብሉይ ኪዳን የተገለጠ እግዚአብሔር በሐዲስ ኪዳን የተገለጠው እሱ እራሱ ነው:: ሁለቱምስለተመረጡ ህዝቦች ይናገራሉ::በብሉይ ኪዳን የተመረጡ ህዝቦች የሚባሉት እስራኤላዊያን(ዘስጋ) ሲሆኑ በሐዲስ ኪዳን የተመረጡ ህዝቦች ክርስቲያኖች(እስራኤል ዘነፋስ) ናቸው::ሁለቱም በቅዱሳን ሰዎች በእግዚአብሔር መሪነት የተጻፉ ናቸው:: የሁለቱን ኪዳናት በምሳሌ ለማስረዳት ይረዳን ዘንድ የሚከተለውን ምሳሌ እንመልከት፡- አንድ ፊልም ሁለት ዲስኮች ቢኖሩት A እና B፤ብሉይ ኪዳን A ስትሆን ሐዲስ ኪዳን B ነች፡፡ አንድ ሰው A ወይም B ብቻ አይቶ ሙሉ ታሪኩን መናገር አንዳማይችል ሁሉ ብሉይ ኪዳንን ሳውቁ ሐዲስ ኪዳን መቀበል አይቻለም እንዲሁም ሐዲስ ኪዳን ተቀብሎ ብሉይ ኪዳን መተው አይቻልም፡፡

3.1.1 የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ክፍሎች
1.የህግ ክፍል (ብሔረ ኦሪት) /Tora/
በሙሴ አማካኝነት የተጻፉ 5 የህግ መጽሐፍቶች በውስጡ ይዟል:: እነርሱም ኦሪት ዘፍጥረት፣ኦሪት ዘጸአት፣ኦሪት ዘሌዋዊያን፣ኦሪትዘኁልቅና ኦሪት ዘዳግም፣ ናቸው::

2.የታሪክ ክፍል (ከቱቢም-kethubim)
1.መጽሐፈ ኢያሱ
2.መጽሐፈ መሳፍንት
3.መጽሐፈ ሩት
4.1ኛ እና 2ኛ ነገስት
5.መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊና ካልዕ
6.1ኛ ዜና መዋዕል
7.2ኛ ዜና መዋዕልና ጸሎተ ምናሴ
8.መጽሐፈ ዕዝራነህምያ
9.መጽሐፈ ዕዝራ ስቱኤል እና መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ
10. መጽሐፈ ጦቢት
11.መጽሐፈ ዮዲት
12.መጽሐፈ አስቴር
13.መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ
14.2ኛና 3ኛ መቃብያን
15.መጽሐፈ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን
16.መጽሐፈ ኩፋሌ
17.መጽሐፈ ሄኖክ
3. የመዝሙርና የጥበብ መጽሐፍት
1. መጽሐፈ ኢዮብ
2. መዝሙረ ዳዊት
3. መጽሐፈ ምሳሌ
4.1ኛ እና 2ኛ ነገስት
5. መጽሐፈ መክብብ
6.መኃልየ መኃልየ ዘሰሎሞን
7.መጽሐፈ ጥበብ
8.መጽሐፈ ሲራክ
4.የትንቢት መጽሐፍት
የትንቢት መጽሐፍት በውስጡ 16 መጽሐፍትን ይዟል፡፡ከአስራ ስድስቱ መካከል አራቱ አቤት ነብያት ሲሆኑ 16ቱ ደግሞ ደቂቀ ነብያት ተብለው ይጠራሉ፡፡

1.ትንቢተ ኢሳይያስ
2.ትንቢተ ኤርሚያስ
3.ትንቢተ ሕዝቅኤል
4.ትንቢተ ዳንኤል
5.ትንቢተ ሆሴዕ
6.ትንቢተ አሞጽ
7.ትንቢተ ሚክያስ
8.ትንቢተ ኢዩኤል
9.ትንቢተ አብድዩ
10.ትንቢተ ዮናስ
11.ትንቢተ ናሆም
12.ትንቢተ ዕንባቆም
13.ትንቢተ ሶፎንያስ
14.ትንቢተ ሀጌ
15.ትንቢተ ዘካርያስ
16.ትንቢተ ሚልክያስ
3.2 የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት ብዛት እና አከፋፈል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤ/ክአቆጣጠር መሠረት የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት ብዛት 35 ነው፡፡ / ፍትሐ ነገስት አንቀጽ 2/ 35ቱ የሐዲስኪዳንመጽሐፍትበ5 ክፍሎች ይክፈላሉ፡፡ አከፋፈላቸው እንዲሚከተለው ነው፡-

- የወንጌል ክፍል---- 4ቱ የወንጌል መጽሐፍት (የማቴዎስ፣ የማርቆስ፣ የሉቃስ እና የዮሐንስ ወንጌል ናቸው፡፡)
- የታሪክ ክፍል---- የሐዋርያት ስራ
- የመልዕክት ክፍል---- 14ቱ የቅዱስ ጳውሎስ፣ 3ቱ የቅዱስ ዮሐንስ፣ 2ቱ የቅዱስ ጴጥሮስ፣ 1 ቅዱስ ይሁዳ እና 1 ቅዱስ ያዕቆብ መልዕክታት ናቸው፡፡ በአጠቃላይ 21 መልክታት
- የትንቢት ክፍል--- የዮሐንስ ራዕይ
- የስርዓት ክፍል---- ስርዓተ ጽዮን፣ ትዕዛዘ ሲኖዶስ፣ ግጽው፣ መጽሐፈ ኪዳን 1 እና 2 መጽሐፈ አብጡሊስ፣ መጽሐፈ ቀሌምንጦስ፣ መጽሐፈ ዲዲስቅልያ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ 8 መጽሐፍት ናቸው፡፡