ክፍለ ትምህርት ፩
- ሥርዓት፡- ማለት ሠርዐ ሠራ ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ደምብ አሠራር መርሀ ግብር ማለት ነ::
- ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፡- የቤ/ክ ዕቅድ፣ የቤ/ክ አሠራር መርሃ ግብር ወይም ደምብ ማለትነው፡፡
በአጠቃላይ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ስንል የቤተክርስቲያን እቅድ ፣ አሰራር ፣ መርሀግብር ወይም ደንብ ማለታችን ነው ፡፡በሌላ በኩል በክርስቶስ ክርስቲያን ተብለን ክርስቶስን የምንከተል የኦርቶዶክስ አማኞች ማህበር ስላለብን ስርአቶችና ስለተደነገጉልን ህጎች እንዴት መጠበቅ እንዳለብን የሚያሳይ ክፍል ነው ፡፡ በአጠቃላይ በአግባቡ ስለ እምነታችን ጠንቅቀን እንድናውቅ የሚያስረዳ ነው ፡፡
1.ቤተ ክርስቲያን፥- ቤተ ክርስቲያን የሚለ ቃል ከሁለት ቃላት የተገኘ ሲሆን ቤት እና ክርስቲያን።
2.ቤት ማለት ማደሪያ መሰብሰቢያ ማለት ነው።
3. ክርስቲያን ማለት በክርስቶስ ያመኑ ምዕመን የሚጠሩበት ስም ነው። በአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያን ማለት የክርስቲያኖች ማሰብሰቢያ ማደሪያ የክርስቲያኖች ቤት ማለት ነው።
ለምን ይጠቅማል?
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን የተለያዩ ምስጢራትን /ጥምቀት፣ቁርባን…./ እና አገልግሎቶች /ፆም፣ ፀሎት፣ስግደት…/ እንዴ እንደምንፈፀም ያሣየናል፣ ይጠቁማል፡፡
የሥርዓተ ቤተክርስቲያን ምንጮች
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን የተለያዩ ምንጮች አሉት፡፡ እነሱም
1.መጻህፍተ ብሉያት
2.መጻህፍተ ሐዲሳት
3.የሐዋርያት ሲኖዶስ
4.ሥርዓተ ጽዮን
5.አብጥሊስ
6.ትዕዛዝ
7.ዲድስቅልያ
8.ፍትሕ መንፈሳዊ
9.የሶስቱ ጉባኤያት ውሳኔዎች( ኒቂያ ፣ ቁስጥንጥንያ ና ኤፌሶን )
10.ሌሎችም ከ አራተኛው ክ/ዘመን በኋላ የተነሱ ሊቃው
- ቤተ-መቅደስ የሚለው ከሁለት ቃላት የተገኘ ነው ፡፡
ቤተ እና መቅደስ
ቤተ ፡-በቁሙ ማደሪያ ፣ መኖሪያ ፣ ስራ መስሪያ ማለት ነው ፡፡ በ ጉባኤ ማህበር (ቤተ-እስራኤል) ቤተ-ክርስቲያን እንዲተካ ነው ፡፡
መቅደስ ፡- ማለት ደግሞ መቀደሻ ፣ ማመስገኛ መስዋእት ማቅረቢያ ማለት ነው ፡፡
- ቤተ-መቅደስ -ቤተ እግዚአብሔር ፣ የእግዚአብሔር ማደርሪያ ፣ የቅዱስ ሥሙ መጠሪያ በቅደስ ኦሪት ፣ መቅደሰ ወንጌል ቤተ-ክርስቲያን ማለት ነው ፡፡ አንድም ቤተ-መቅደስ ማህበረ እግዚአብሔር ጉባዔ ምዕመናን የሚለው ትርጉም ሲወስድ ክርስቲያኖች ራሳቸው ማህደረ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር ማደሪያ) መሆናቸውን ያሳያል ።
የቤተ ክርስቲያን ትርጉም
ቤተ-ክርስቲያን የሚለው ቃል እንደ አባቶቻችን አስተምሮ በ 3 አይነት ፍቺ ይተረጎማል ፡፡
1.የክርስቲያን አንድነት(ጉባኤ ምዕመናን)
2.እያንዳንዱ ክርስቲያን ቤተ-መቅደስ ይባላል
3.ሕንጻ ኤተ ክርስቲያን
1)የክርስቲያን አንድነት (ጉባኤ ምዕመናን) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሁለትም ሦስትም ሆነው በሥሜ በሚሰበሰቡት እኔ በመሀከላቸ ው እገኛለው” ማቴ16÷20 ባለው መሰረት የምዕመናን ጉባኤ ቤተ ክርስቲያን ይባላል ፡፡1ኛ ቆሮ11÷16
2)ክርስቲያን ወይም ምዕመናን ፡- እያንዳንዱ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ማደሪያ ነው ፡፡ የእግዚአብሔር ቤተ-መቅደስ እንደሆናቸው የእግዚአብሔር መቅደስ መሆናአውን አታውቁምን በሌላ በኩልም 1ኛቆሮ6÷19 “ወይስ ሥጋቹሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ-መቅደስ እንዳለ አታውቁምን” ይህ የእያንዳንዱ ክርስቲያን መሰረተ ቤተ- መቅደስ እንደሆነ ይነግረናል ፡፡
3)ህንፃ ቤተ-ክርስቲያን ፡- እግዚአብሔር የሚመለክበት ፣ መስዋዕተ ወንጌል የሚሰዋባቸው ክርስቲያኖች የሚሰበሰቡበት ቤት ቤተ-መቅደስ ተብሎ ይጠራል ይኸው ቤት ቤተ-መቅደስ የሚባለው የምስጋና ቦታ ስለሆነ ነው ፡፡ በቅዱሳት መፃህፍት ህንፃ ቤተ-ክርስቲያን ህንፃ መሆኑ ተገልፆል ፡፡ 2ኛዜና7÷12-15 ይኸውም እኔ ለዘላለም ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለው አይኖቼና ልቤ ዘወትር ከዚህ የኖራሉ ተብሎ እንደተናገረው ፡፡
የቤተክርስቲያን አሠራር
የቤተክርስቲያን ሥራ ፈቃድ
ቤተክርስቲያን ለመትከል ለመስራት ሲያስፈልግ የክልሉን ኤጲስቆዾስ ማስፈቀድ ያስፈልጋል ያለ ኤጲስቆስዾስ ፈቃድ ቤተ ክርስቲያን አይተከልም ወይም አይሰራም ፡፡ፍትሐመን(1÷3)
ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ናትና በግለሰቦች ፈቃድ እንዲሁም ስምምነት አትተከልም እራሱ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያሰሩና እንዲፈቱ ፈቃድንም አውቀው እንዲፈጽሙ ስልጣኑንም ጸጋውንም የሰጣቸው ዻዻሳት መፍቀድ አለባቸው ፡፡ ፡- ይህም የእነርሱ ግለሰባዊ ፈቃድ ሳይሆን ፈቃደ እግዚአብሔር የሚታወቅበት በስርአት ለመኖራችን መገለጫ ነው ፡፡
የቤተ ክርስቲያን አሠራር
ሶስት አይነነት የቤተክርስቲያንአሠራር አለ፡፡ እነሱም ፦
1. ሰቀላ (ሞላላ)፡ እንደ ብሉይ ኪዳን ቤተ መቅደስ(ምኩራብ) ቅርጽ ያለው ነው። ውስጡ በመጋረጃ ወይም በአእማድ እንጂ በግንብ የተከፈለ አይደለም። የዚህ ዓይነት ቤተክርስቲያን ቅርጽ የተወረሰው ከሰሎሞን ቤተመቅደስና ኋላም በዘመነ ክርስትና ታላቁ ቆስጠንጢኖስና እናቱ ዕሌኒ በኢየሩሳሌም በቤተልሔም ካሰሩዋቸው የተወሰደ ነው። የሰቀላ ቤተክርስቲያን በሩ የተወሰነ አይደለም ሶስትም አራትም ከዚያም በላይ ሊሆን ይችላል። የሰቀላ ቤተክርስቲያን ጉልላቱ እንደ ቤተክርስቲያኑ ትልቀት ከአንድ በላይ ሊሆን ይችላል።
2. ቤተ-ንጉስ (ክብ)፡ ዙሪያው ክብ የሆነና በግድግዳ ከሶስት ይከፈላል። የመጀመርያው ክፍል ቅኔ ማህሌት፣ ሁለተኛው ክፍል ቅድስት፣ ሶስተኛው ክፍል መቅደስ ይባላል። የዚህ አይነት ቤተክርስቲያን አንድ ጉልላት ብቻ ይኖረዋል።
ቤተ ንጉሥ ይባላል፡- ምክንያቱም የቀድሞ ነገስታት በመንግስታቸው በራሳቸው ዘውድ ይደፉ ስለነበር ቤታቸውም ላይ ምልክት ያደርጉ ስለነበር ህንፃ ቤተክርስቲያን ሲሰሩ እኛ ምድራዊ ነገስታት ስልጣናችንም ሀላፊ ነው አንተ ግን ዘላለማዊ ንጉስ ስለሆንክ እንዲያለ ያማረ ቅርጽ ያለው ቤተ-መቅደስ ይገባሀል እያሉ ይሰሩ ነበር። ቤተክርስቲያን ሲሰራ ሙሉ በሙሉ ክብር መሆን ፍጹምነትን ያመለክታል።
3. ዋሻ፡ በሩ አንድ ብቻ ነው። ክፍሎቹ(ቅኔ ማህሌት፣ ቅድስት፣ መቅደስ) የሚለዩት በመጋረጃ ነው። የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ምሳሌ ይሆናሉ። ጉልላት የለውም።
አንድ የሚሆኑበት
-ቅኔ ማህሌት፣ቅድስትና ምቅደስ አላቸው፡፡
-በውስጣቸው የሚፈጸመሙ የቅዳሴ የማህሌት የስርአተ ጸሎት አንድ ነው፡፡
የሚለያዩበት
-ሰቀላማና ክብ ቅርጽ አብያተ መቅደስ ከጉልላት ስፍራቸው ዋሻ ቅርጽ ቤተ-መቅደስ ጉልላት የለውም ።
-ሰቀላማና ዋሻ ቅርጽአብያተ መቅደስ የውስጥ ክፍሎች የሚከፋፈሉት በመጋረጃና ወለሉን ከፍ በማድረግ ሲሆን ክብ ቅርጽ ግን በግድግዳ ይከፋፈላል ፡፡
-በሰቀላማና ዋሻ ቅርጽ አብያተ መቅደስ የሴትና የወንድ መቆሚያ በመጋረጃ ሲሆን ክብ ቅርጽ ግን በተለያዩ ቦታ ሆነው ያስቀድሳሉ ፡፡