Advertisement Image

ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

መሰረታዊ የክርስትና ትምህርቶች እና ትንታኔዎች

የሥርዓተ ቤተክርስቲያን ምዕራፎች

ክፍለ ትምህርት ፬ : ወደ ቤተ-መቅደስ ለመግባት መደረግ የሚገባው ዝግጅቶች

ወደ ቤተ-መቅደስ ለመሄድ የሚነሳ ሠውእግሩን መጠበቅ ማለትም እግረ ስራውን ከማይገባ ቦታ እግረ ህሊናውን ከሀጢያተ ከበደል መጠበቅ ይገባዋል ፡፡ መቼ እንዴት ሆኖ ወደ ቤተ-መቅደስ (ቅድመ እግዚአብሔር) መግባት እንዳለበት ማወቅና አስቀድሞ መዘጋጀት ይኖርበታል ፡፡ ወደ ቤተ-መቅደስ ከመግባት አስቀድሞ ሊደገረጉ የሚገቡ ዝግጅቶች ፡-

1.የልቦና ዝግጅት ፡- ወደ ቤተ-መቅደስ ለመሄድ ከመነሳታችን በፊት ልቦናን ከቂም ፣ ከበቀል ፣ ከክፋት ፣ ከተንኮክ ፣ ከጦኦት አመምልኮ ፣ ከዝሙት ንፁህ ማድረግ አለብን ምክንያቱም ራሳችንን ካልመረመርን ልብና ኩላሊት የሚመረምርእግዚአብሔር ሊመረምረን ሊንቀንም ይችላል ፡፡ መዝ 7÷9 ፣ መዝ 50÷17 “የእግዚአብሔር መስዋዕት የተከበረ መንፈስ ነው” ”የተሰወረውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም” ማቴ 5÷8 ልበ ንፁሀን ብፁአን ናቸው እግዚአብሔር ያዩታልና ተብሎ እንደተነገረው እግዚአብሔር ከምናከርበው መባ (ስጦታ) እና ከስለታችን በፊት እና በዋላ የልባችንን ቅንነት ይመለከታል ፡፡ ዘፍ 4÷4 እግዚአብሔር ወደ አቤልና መስዋዕቱ ተመለከተ፡፡

2.ንፁህ ልብስ መልበስ ፡- ቤተ-መቅደስ መልካም መአዛ ያለው እጣን ለእግዚአብሔር የሚቀርብበት ምዕመናን የልባቸው መሻት የከንፈራቸው ፍሬ የሆነ ፀሎታቸው የሚያቀርቡበት የሀዲስ ኪዳን በግ የጌታችን የመዳኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰዋበት ንፁህ የሰርግ ቤት ነው ፡፡በዚህ ቤት ለሰው ልጆች ነፍስና ስጋ ላይ የሚፈርደው የጌቶች ጌታ የነገስታት ንጉስ እግዚአብሔር አለ ፡፡በዚህ ቤት በስራም በነፍስም ንፅህት የሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ቅዱሳኑ አሉ ፡፡ ከዚህ አንፃር ለማንኛውም አገልግሎት ወደ ቤተ-እግዚአብሔር ስንሄድ ለምድራዊ ሰርግ ቤት ለአለባበሳችን እንደምንጨነቀው ሁሉ ለሠማያዊው ሰርግ ቤት በንጉስ አምላክ ፊት እንደምንቆም ከቅዱሳን ጋርም እንደምንታይም አስበን ያንን ልብስ ንፁሀጅ አድርገን መሔድ ይገባል ፡፡ ዘፍ33÷2 “እንግዶቹን አማልክት ከመካከላቸው አስወግዶ ንፁህንም ሁሉ ልብሳቸውንም ለውጡ ተነስተንም ወደ ቤት ኤል እንወጣ በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ በሔድኩበትም መንገድ ከኔ ጋር ለነበረው ለእግዚአብሔር መሰውያን አደርጋለው ፡፡” ብሎ ያዕቆብ ተናግሯል ፡፡ ስለዚህ ወደ ቤተ-መቅደስ 2.በምንሄድበት ቀን ወደ ስራ ገበታችን እና ወደ ሰርግ ቤት ስንሄድ ከምንዘጋጀው በላይ ተዘጋጅተን ጸአዳ ለብሰን ሰውነታችንን ንፁህ አድርገን መሄድ ይኖርብናል ፡፡

3.ነጠላ ወይም ጋቢ አደግድገን በትምርተ መስቀል መልበስ ፡-ወደ ቤተ-መቅደስ ስንሄድ ነጭ መልበሳችን የተገባ ነው ፡፡ ነጭ ነጠላ ወይም ጋቢ ወደ ግራና ወደ ቀኝ በትምዕርተ መስቀል አጣፍተን የምንለብሰው ክርስቶስ በቀራንዮ በመስቀል መሰቀሉን ወይም የተቀበለውን መከራዎች ለማሰብ ነው ፡፡ ነጭ ልብስ ወይም ነጠላ የምንለብስበት ምክንያት በዚህ ምድር ላይ በብዙ መከራ ተፈትነው ያሳለፉና በክብር የበቁ ቅድሳን በሰማያት የክብርና የቅድስና ምስክር ወይም መገለጫ ነጭ ልብስ ይሰጣቸዋል ማለትም ብርሃንን ይለብሳሉ እኛም የሚጣብቀንን ሰማያዊ ክብር በማሰብ ነው ነጭ ልብስ እንለብሳለን ፡፡ ዩሐ ራዕ4÷4 ፣ ዩሐራዕ6÷9-11፣ራዕ7÷9 ከዚህም በተጨማሪ ነጭ ስንለብስ ብርሃንን የለበሱ ቅዱሳን ከኛ ጋር እንዳሉና በዙሪያችን ሆነው ስለኛ እንደሚያማልዱ እናስባለን ፡፡ ዕብ12÷1 ቅዱሳን መላዕክት ከኛ ጋር መሆናቸው ለማሰብ ከጌታችን ጋር እንዳለን እንድናስብ ነጭ ልብስ እንለብሳለን ፡፡ለምሳሌ ጌታችን መዳኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ ወቅት ለመቅደላዊት ማርያም ሁለት ነጫጭ ልብስ የለበሱ መላዕክት “ህያውን ከሙታን መካከል ለምን ትፈልጉታላችሁ ተነስቷል አትርሲ” ብለዋታል ፡፡

4.መባ ወይም ስጦታ ይዞ መቅረብ ፡- ይዞ መግባት እንደሚገባ የሚያዘን ህግ የሰራው እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን በሙሴ አድሮ ነው ፡፡ ኦዘጻ25÷1 በሀዲስ ኪዳንም ጌታችን ስለ መባ ሲያስተምር ማቴ5÷23-24 መባውን ቀማቅረባችን በፊት ከቂም ከበቀል ልቦናችንን ማንፃት ፣ከወንድም ከእህቶቻችን ጋር መታረቅ እንዳለብን ያስረዳናል ፡፡ ወደ ቤተ-እግዚአብሔር ስንሄድ ማቅረብ ከሚገባን ስጦታዎቸ መካከል ሻማ፣ጧፍ፣እጣን፣ዘቢብ፣መጋረጃ፣ጥላ፣ምንጣፍ….ይጠቀሳሉ ፡፡ አባታችን አብርሃም በመልከፄድቅ ፊት በቀረበ ጊዜ መልከፄድቅ የጌታችን ስጋና ደም ምሳሌ የሆነውን ህብስትና ወይን አቀበለው ፡፡ አብርሃም ደግሞ ከሁሉ ብሉ አስራትን ለመልከፄድቅ ስጠው ዘፍ14÷17 ካህናት እንደ መልከፄድቅ ሥርአት ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን ሲያቀብሉን ምዕመኑ ደግሞ እንደ አብርሃም አስራት በኩራቱን በቤተ-እግዚአብሔር ያቀርባል ፡፡ ከአበው የወረደ ከእግዚአብሔር የታዘዘ ነውና ስለዚህ ያስታውስን እለት በአጋጣሚ ድንገት ሰው ሲያደተርግ ስላየን ሳይሆን ትዕዛዝ መሆኑን አስበን ወደ ቤተ-መቅደስ ስንሄድ የቻልነውን ተገቢ የሆነውን መባዕ የዘን መሄድ ይገባናል ፡፡

5.በትምርተ መስቀል አማትበን ደጀ ሰላሙን መሳለም ፡-

ሀ) ማማተብ፡- ለጃፍን ለመሳለም ስንቀርብ አስቀድመን በመስቀል አምሳል እናማትባለን ይኸውም መንፈሳዊ የማማተብ መንፈሳዊ ትርጉም ጣቶቻችንን በትምዕርተ መስቀል ካመሳቀልን በኋላ ከላይ ወደ ታች (ከግንባራችን ወደ ደረታችን ) እናወርዳለን ይኸውም ወልደ እግዚአብሔር ከሰማየ ሰማያት መውረዱን ለማመልከት ነው ፡፡በመቀጠል ጣቶቻችን ነው ወደ ግራ ተከሻችን ደስደን መልሰን ወደ ቀኝ ትከሻችን እናመጣቸዋለን ፡፡ከሰማየ ሰማያት አካሉ ወይም በተወላዲነት ግብር የወረደው ቃል እግዚአብሔር ወልድ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ግራ (ወደ ሲኦል) በአካለ ነፍስ እንደወረደና ነፍሳት ወደ ቀኝ (ወደ ገነት)እንዳሻገረ ለማመልከት ነው ፡፡ በአጠቃላይ በሚስጢረ ሥጋዌ የተፈፀመልንን የድህነት ስራ እንመለከታለን አንድም ከግራ ቁመት ወደ ቀኝ ቁመት መለስን ማለት ስናማትብ የምናስባቸው ሚስጢራተ

- ጌታችን ስለመዳናችን በመስቀል ላይ እንደሞተልን እንመለከታለን ፡፡
- እግዚአብሔር ለኛ ያለውን ፍቅር እናስባለን ፡፡ዩሐ15÷13
- የሀጢአት ደመወዝ ሞት እንደሆነ እናስባለን ፡፡ ኤፌ2÷5
- መስቀል ሀይላችን እንደሆነ እናስባለን ፡፡ 1ኛቆሮ1÷18
- ጠላታችንን (ዲያቢሎስን፣አጋንንት) እናስፈራበታለን ፡፡ ሰለኛ የተሰቀለውን የመዳኔአለም ክርስቶስ ተከታዮች መሆናችንን እንመሰክራለን በመስቀል ስናማትብ መስቀሉን በአንገታችን አስረን ፣ በሰወውነታችን በልብሳችን ጠግረን እና ለብሰን ስንታይ ክርስቶስን ማመናችንን እንመሰክራለን ፡፡ የሚመለከቱን ሁሉ በተሰቀለው በእርሱ እንደምናምን ይረዳሉ ፡፡ማቴ10÷32፣ምሳ6÷20

ለ) ደጃፍን መሳለም ፡- የምንሳለምበት የተለያዩ ምሳሌዎች አሉን ፡፡ ቤተ-መቅደስ እንዲሁም በውስጡእና በዙሪያው ያለውን የነካ ሰለሚቀደስ ምክንያቱም ህንፃ ቤተክርስቲያኑ ደጃፍ በቅብአ ሜሮን የከበረ፣የተቀደሰ ስለሆነ የሚሳለመው ወይም የሚስመው (የሚተባበሰው)ሁሉ የቀደስበታል ፡፡ ቤተ-መቅደስ የክርስቶስ ማደሪያ ስለሆነ ኤፌ5÷23 “ስለዚህ አፅዷ በትፅረ ቤተ-ክርስቲያን ያለው ፀበል አጥሩ ፣ቅፅሩ ውስጡ ውጪው ሁሉ ፈውስና መዳኒት ይሆናል ፡፡ ምክንያቱም የልብሱን ዘፈፍ በመንካት እንደተፈወሰችው ሴት የእምነት ጥንካሬ ምልክት ነውና ፡፡

- ቤተ-መቅደስ የመለኮት ማሪያ ስለሆነ 2ኛዜና7÷7
- በዚህም ምክንያት ደጃፍ ፣ አጥሩ፣ቅጥሩ ሁሉ የተቀደሰ በበረከት የተሞላ ነው ፡፡ ስለዚህ አማኞች ቤተ-ክርስቲያንን ደጃፍን“ሰላም ለኪ ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ሀምሳ ለ ኢያሩሳሌም ማህደረ መለኮት ሰማያዊት ቅድስት የምትሆኝ የሰማያዊት ኢየሩሳሌም አምሳል የሆንሽ ቤተ-ክርስቲያን ሆይ የመለኮት ማደሪያ

6.በቤተ-መቅደሱ (በህንፃው) ፊት መስገድ ፡- ወደ ቤተ-መቅደስ ለፀሎት የሚገባ ሰው ደጃፉን ከተሳለመ በኃላ በውስጥ በቤ-መቅደስ ለእግዚአብሔር የአምልኮ (የባህሪ)ስግደት ሊሰግድ ይገባዋል ፡፡ ዘጸ33÷7 ፣ 2ኛዜና7÷3፣ 2ኛሳሙ12÷20፣ መዝ5÷7 “እኔ ግን በምህረትህ በዛት ወደ ቤትህ እገባለው አንተንም በመፍራት ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለው”በቤተ-መቅደስ ተገኝተን ፈጥሮ በማገዛ ለሚመግብ አምላክ የሚገባውን ክብር ብንሰጥ ፣ ብንሰግድ ፣ ብንፀልይ ቤታችን በበረከት ይሞላል እድሜያችን የረዝማል ፣ ልጆቻችን ይባረካሉ ከሁሉም በላይ ለዘላለማዊ ህይወት አድመኞች እንሆናን ፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ለጣኦት ቤት ከተንበረከክን ሰዎች ላቆሙአቸው ጣኦታት ፣ ለቃልአቻ ፣ ለጠንቋይ …ከሰገድን ደግሞ ኑሮአችን የተመሰቃቀለ እድሜያችን ያጠረ የሆናል ፡፡1ኛነገ11÷11

7.በቤተ-መቅደስ ዙሪያ የሚገኙ ቅዱሳት ስዕላት እጅ መንሳት፦ ቅዱሳን ስዕላት በቤተ-መቅደስ እንዲሳሉ እና እንዲቀመጡ እንዲሰገድላቸው ያእቀደ እግዚአብሔር ነው ፡፡ንጉስ ሰሎሞን ቤተ-መቅደስ ሲሰራ በውስጥና በውጪ የቅዱሳን ስዕል እንደቀረፀ በወርቅ እየለበጠም እንዳስ ጌታችን እናያለን ህዝቡም በቤተ-መቅደሱ ሲሰማዱ፣ለቅዱሳን ስዕላትም እንደሰገዱ ያመለክታል ፡፡እግዚአብሔርም በቅዱሳን ስዕላቱ አማካኝነት ክብሩን ይገልጥ እንደነበር ያስረዳል ፡፡ የተቀረፀውን ምስል ለአንተ አታድርግ የተባለው አህዛብ ለሚያቆሙት ጣኦት አትስገድ በማለት እንጂ በቀደሰው ስዕል አትስገድ ማለቱ አይደለም ፡፡ ምክንያቱም ሙሴን እና ጠቢቡ ሰለሞንን ቅዱስ ስዕላቱን በቤተ-መቅደስ ሲያስቀርፁ እግዚአብሔር ዝም ባላለ ክብሩንም በቅዱሳት ስዕላቱ ላይ ባልገለፀ ነበር ፡፡ዘፀ25÷22፣1ኛ ነገ6÷23-29 እግዚአብሔርንም ሰዎችን ለማዳን እንኳን በቤቱ የተሳሉ ቅዱሳን ስዕላትን ቀርቶ ሌሎችንም ግኡዛን ፍጥረታትን ሊጠቀምላቸው ይችላል ፡፡ ለምሳሌ፡-ዘሁ21÷8-9 የሙሴ የነሀስ እባብ ሰቅሎ እስራኤላወያንን ከታዘዘባቸው መቅሰፍት ድነዋል ፡፡ዘፀ14÷15 ህዝበ እስራኤላያን ባህረ ኤርትራን ተሸግረው ከጠላት ሲድኑ ሙሴ ባህሩን የከፈለው በያዘው በትር ነበር ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር በነዚ ሁሉ ላይ አድሮ ታምራቱን ካደረገ በቅዱሳን ስዕላቱ ላይ አድሮ ድንቅ ሥራውን እንዳይሰራ የሚከለክለው ማነው?ቅድስት አፎምያም ከዳቢሎስ ያዳናቸው ቅዱስ ሚካኤልን ይዛ ነው ፡፡

በቤተ-መቅደስ የተከለከሉ ነገሮች
1)ጫማ አድርጎ ወደ ቤተ-መቅደስ መግባት ፡-ዘፀ3÷5 ላይ “አንተ የቆምክብት ስፍራ የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግር አውልቅ ብሎ እግዚአብሔር ለሙሴ እንተናገረው በዚህም በእግረ ሥራው ላይ ጫማውን እንዲፈታም ከእግረ ልቦናውም ልማድ እንዲያጠፋ ተነገረውእግዚአብሔርም ይህንን ያደረገው ፈልጎ ነው ፡፡ ለህዝበ እስራኤላውያን ህጉን እንዲያስተላልፍላቸውፈልጎ ነው ፡፡ ስለዚህ በልቦናው የነገሰውን እያስወገደ በአፍአ የእግረሩን ጫማ አውልቋል ፡፡ በዚህም መሰረት ታቦተ ህጉ ላለበት የክርስቶስ ስጋና ደም በሚፈተትበት ቃለ እግዚአብሔር በሚነገርበት ቤተ-መቅደስ ጫማን አድርጐ መግባት ክልክል ነው ፡፡ ሙሴ ሐመልማሉ ከነበልባሉ ተዋህዶ ሲነድ ያየበት ደብረ ሲና የተቀደሰ ቦታ (ስፍራ) እንደሆነ ሁሉ የእግዚአብሔር ቤት 1)የሚታነፅበት ቦታ ሁሉ ቅዱስ ነው ፡፡ 2ኛዜ.መ7÷14 “አሁንም ስሜ ለዘላለም በዚህ ይኖር ዘንድ ይህንን ቤት መርጫለው ቀድሻለው ”እንዲል ስለዚህ መስዋዕት በሚሰዋበት ቃለ እግዚአብሔር በሚነገርበት ታቦተ ህጉ ወዳለበት ቅዱሳን መላዕክት ወደ ሚዘምሩበት ስፍራ ስንገባ በውስጥ የሀጢአተን ጫማ ማውለቅ ይገባናል ፡፡

2)በቤተ-ክርስቲያን አፅድ ስጋዊ ግበዛ ማድረግ አይገባም ፡- የክርስቶስ ስጋና ደም ከሚሰዋበት ምዕመናን ስጋና ደሙን ከሚቀበሉበት ከቤተ-ክርስቲያኑ ራቅ ብሎ በደጀ ሰላም (በቤተ-ምርፋቅ) ካልሆነ በስተቀር በቤተ-መቅደስ ውስጥና በአውደምግረቱ ላይ ስጋዊ መብልና መጠጥ ማቅረብ መብላትና መጠጣት አይገባም ፡፡ ፍትሃ ነገ 1ቁጥር 12 ላይ

3)የቤተ-ክርስቲያን መገልገያ ነዋየ ቅዱሳትን ለግል ጥቅም ማዋል አይገባም ፡-በቤተ-ክርስቲያን የምሰትገለገሉባቸው እያንዳንዳቸው ነዋያት የተቀደሱ ናቸው ፡፡ ስለዚህ እነዚህ የተቀደሱ ነዋያት ለእግዚአብሔር አገልግሎት ማቅረቢያነት በቤተ-መቅደስ የቀመጣሉ አስፈላጊ ለሆነ ሰአትም ካህናት ለአገልግሎት ሊጠቀሙባቸው ከቤተ-ክርስቲያኑ ይዘው መውጣት ይችላሉ ፡፡ ለምሳሌ ፡-ከበሮ፣ፅናፅልቋሚያ…ለቤተ-ክርስቲያን መብአ ሆኖ የተሰጠ ሁሉ ለግለሰብ መጠቀሚያ መሆን የለበትም በአራጣ መበደር ፣ በወርቅ መጠቀም፣ በንዋያቱ ፈትፍቶ ነብላትና መጠጣት በእግዚአብሔር ዘንድ አፀያፊ ነው ፡፡ ትን.ዳ 5÷2-5 ከልጣሰርም የወይን ጠጅ በቀመሰ ጊዜ ንጉስና መኳንንቶቹ ሚስቶቹና ቀባቶቹ የጠጡላቸው ዘንድ ፡፡ በፍትሀ ነገስት አንቀፅ 1 ላይም ከቤተ-ክርስቲያን የተባረከ እቃ ወገን የሆነውን ሁሉ ወርቅና ብር እቃም ቢሆን ሰው በቤቱ ውስጥ ሊሰራባቸው አይገባም፡፡ ይህ ህግን ማፍረስ ነውና ፡፡ ይህንን ያደረገ እንዲሁም የተፈረደበት በኋላ ከቤተ-ክርስቲያን ይለይ ፡፡

>4)በቅፅረ ቤተ-ክርስቲያን መገበያየት አይገባም ፡- በቤተ-ክርስቲያን አደባባይ መፀለይ ፣ በቁረብ፣ ቃለ እግዚአብሔርን መስማት ፣ መዘመር እንጂ ስጋዊ ንግድ መነገድ አይፈቀድም ፡፡ በውስጥ በአፅዷም ሆነ በውጪ በአፍ በሮች አጠገብ መሸጥ መለወጥ የሰው ህሊና ስጋዊ ቁሳቁስ እያሳዩ መጥረፍ አይፈቀድም ፡፡ ሁሉን መከልከል ቢያቅተን ቢያንስ ከመግዛት (ከመገበያየት)መታቀብ ይኖርብናል ፡፡ ዩሐ2÷ ቤቴ የፀሎት ቤት ይባላል እናተ ግን የወንበዶዋች ዋሻ አደረጋችሁት እንደተባለው ፡፡ ይህ ሲባል ግን ገዳማቱ (አድባራቱ) ምዕመናን እንዲጠቀሙበት የሚቀርቡት ጧፍ፣ እጣን ፣ ሻማ እና የመሳሰሉትን አይመለከትም ፡፡

5)በቤተ-መቅደስ በማህበር ፀሎት ወቅት የግል ፀሎት ማድረግ ክልክል ነው ፡-መዝ 132÷1 “ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ እነሆ መልካም ነው እነሆም መልካም ነው” እንዲል በህብረት መፀለይ መዘመርና መማር መልካም ነው ሐዋርያትም ተሰብስበው ይፀልዩ እንደነበረው ፡፡ ለምሳሌ ፡- በቅዳሴ፣በኪዳን እንዲሁም በሌሎች የአንድነት ፀሎት የሚችል ተሰጥኦውን መመለስ የማይችል በአርምሞ ሆኖ ስርአቱን መከታተል (መሣተፍ) ይኖርበታል እንጂ የግል ፀሎት ማድረግ አይፈቀድም ነገር ግን በሰላም ግቡ ብሎመ ካሰናበተ በኋላ መፀለይ ይቻላል ፡፡ቅዳሴ እየተቀደሰ በሌላ መፅሀፍ መፀለይ ለጠራራ ፀሀይ ሻማ ለኩሶ (መብራት ይዞ) እንደመሄድ ይቆጠራል ፡፡ከህብረት ፀሎት ይልቅ የኔ ፀሎት ይበልጣል ብሎ እንደማቅለል የቆጠራል ፡፡ እንዲህ የተባለበት ምክንያት ቅዱሳን ይኖራሉና ስለ እነርሱ ፈንታ ይቅር በለኝ በማለት ፈንታ የኔ የራሴ ልድንም ማለት ከዚህ ህዝብ እኔ እሻላላው እንደማለት ይሆናል ፡፡

6)በቤተ-መቅደስ በቅዳሴ ሰዓት አቋርጦ መውጣትክልክል ነው ፡- በቤተ-መቅደስ የሚፀለዩ ፀሎቶች በሙሉ አርምሞ(ትግስትን) የሚፈልጉ ናቸው ፡፡ ስለዚህ እነዚህን ፀሎቶች አቋርጠን መውጣት የለብንም ፡፡

7)ሴት ልጅ የወር አበባ ወቅት ላይ ወደ ቤተ-መቅደስ መሄድ የለባትም ፡፡ ዘሌ12÷16

8)ወንድ ልጅ ህልመሌሊት (ዝንያት) ከመታው ወደ ቤተ-መቅደስ መግባት አይችልም ዘሌ15÷2-18 ከአንድ ቀን በኋላ ሰውነቱን ታጥቦ መግባት ይችላል ፡፡

9)የለሊት ልብስ ወይም የአረማውያን ልብስ ለብሶ ወደ ቤተ-መቅደስ መግባት ክልክል ነው ፡፡ የቤተ-መቅደሱን ክብር ያሳንሰዋል ምክንያቱም የለሊት ልብስ በተለያዩ ነገሮች ሊተሸሽ ይችላል ፡፡ ዘፍ9÷21-27፣ዘሌ19÷10-11፣1ኛቆሮ11÷5-14

10)ባልና ሚስት ከተራከቦ በኋላ ዕለቱን ወደ ቤተ-መቅደስ መግባት አይፈቀድላቸውም ፡፡1ኛቆሮ7÷5፣ዘፀ19÷15

>11)በቤተ-መቅደስ ውስጥ መሣቅ መሣለቅ ዋዛ ፈዛዛ ነገር ማውራት ክልክል ነው ፡፡ ታላቅ የቤተ-ክርስቲያን አባት ዩሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ብሏል የምትስቁበትን ክፉ ነገርን ሁሉን ከልቦናችው አርቁ፤ዛሬ የምትስቁ ሰዎች ኋላ ታለቅሳላችውና ወየውናችሁ ፡፡

12)አብዝቶ ጠጥቶና ሰክሮ መግባት ክልክል ነው ፡፡ ዘሌ10÷8-10፣ዘፍ8÷10

የቤተክርስቲያን ዋና ዋና የአገልግሎት አይነቶች
1.ሠዓታት፡- ሰዓታት ማለት በየሰዓቱ የሚጸለይ ሰዓቶችን ተመልክቶ የሚቀርብ ጸሎት ማለት ነው፡፡በአብዛኛው በዓብይ ፆም እና በፆመ ፍልሠታ ወቅት በሌሊት የሚደርስ ፀሎት ነው፡፡ በጥቂት ገዳማት ና አድባራት ከአመት እስከ አመት ይቆማል፡፡ በዋናነት በሌሊት የሚደርስ ሆኖ ነገር ግን ከሁለት በመክፈል የቀንና የሌሊት ተብሎ ይታወቃል፡፡ይህ ጸሎት በአባ ጊዮርጊስዘጋስጫ የተደረሰ ነው፡፡

2.ማህሌት፡- በበዓላት ቀን የሚደርስ የመዝሙር ምስጋና ነው፡፡ በጌታችንና በእመቤታችን በዓላት ቀን በሁሉም አድባራት እና ገዳማት ማህሌት የሚቆም ሲሆን በሌሎች በዓላት ግን ታቦቱ ባለበት ቦታ ማህሌት ይቆማል፡፡ ለምሳሌ፡- በደብራችን የኢየሱስ በዓል ሲሆን ጥር 6 እና የዕርገት እለት ማህሌት ይቆማል፡፡ የእመቤታችን በዓላት ደግሞ ህዳር 21 ጥር 21 እና ሰኔ 21 እንዲሁም ታህሣሥ 3 ቀን ማህሌት ይቆማል፡፡ በእነዚህ በዓላት ቀን ማህሌቱ የሚጀምረው ከዋዜማው ነው፡፡ ለምሳሌ የህዳር ፅዮን በዓል ማህሌት የሚጀምረው ህዳር 20 ከቀኑ 7 ሰዓት ሲሆን እስከ 10 ወይም 11 ሠዓት ይዘመራል፡፡ ይህ ዋዜማ ይባላል፡፡ ከዚያም ከምሽቱ 3 ሰዓት ሲሆን ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12 ሠዓት ይዘመራል፡፡ ፆም ከሆነ ግን ከሌሊቱ 5 ወይም 6 ሰዓት ጀምሮ የሚቀጥለው ቀን (በበዓሉ ቀን) ታቦት እስከሚወጣ ይዘመራል፡፡

3. ቅዳሴ፡- ይህ ስርዓት ቤተክርስቲያን የምእመናን አንድነት ናት የሚለውን የሚያመለክትልን ስርዓት ነው። የቤተክርስቲያን ሁሉም አገልግሎት የሚያልቁት ቅዳሴ ተቀድሶ ምዕመናን ስጋ ወደሙ ከተቀበሉ በኋላ ነው፡፡ በፆም ወቅት እንዲሁም ረቡዕ እና አርብ ቅዳሴ ከሠዓት 6 ሠዓት ተጀምሮ 9 ሠዓት ይጠናቀቃል፡፡ በሌሎች ቀናት ግን ከጠዋቱ 12 ሠዓት እስከ 2 ወይም 3 ሠዓት ይቆያል፡፡

ጸሎተ ቅዳሴው ሶስት ታላላቅ ክፍሎች አሉት። እነርሱም ፡
ሀ) ግብዓተ መንጦላይት(የዝግጅት ቅዳሴ)
ለ) የንባብ (የትምህርት) ቅዳሴ
ሐ) ፍሬ ቅዳሴ