ምዕራፍ ሦስት : አማናዊት ቤተ-ክርስቲያን
3.1 ቤተክርስቲያን በክርስቶስ መመስረት
ቅዱስ ጳውሎስ እንደጻፈው “የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እኛ ልጆቹ እንሆን ዘንድ ከሕግ በታች ያሉትንም ይዋጅ ዘንድ እግዚአብሔር አብ ከሴት የተወለደውን ለሕግ ታዛዥ የሆነውን ልጁን ላከልን፡፡” ገላ 4÷4 ይህም የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አለምን ሁሉ ከኃጢአት ከመርገም ይዋጅ ዘንድና የእውነት ፣ የፍቅርና የሰላም መንግስትንም ለሚያምኑበት ሁሉ ይመሰርት ዘንድ ነው፡፡[የእግዚአብሔር መንግስት ታሪክ በአለም ላይ ገጽ ] በሰው ልጆች መካከል ልዩነትን የማታደርግ የሰውን የመንፈስ ጥም የምታረካና ከእግዚአብሔር ልጅነትን የምታሰጥ እውነተኛይቱን የክርስትና ሐይማኖት ለመመስረት የጥል ግድግዳ ሊያፈርስ በነቢያት የተነገረውን ትንቢት ሊፈጽም አካላዊ ቃል ስጋ ሊሆን ከእኛ ጋራ ሊዋሐድ ከሰማየ ሰማያት ወረደ፡፡[የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ ] የአለም መድኅን የሆነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደቡባዊ የይሁዳ ክፍል ልዩ ስሟ ቤተልሔም በተባለችው ስፍራ ሄሮድስ በይሁዳ በነገሠበት ዘመን ተወለደ፡፡ ሰብአ ሰገል ለተወለደው ህፃን ለንጉሥ የሚገባውን እጅ መንሻ ሲያቀርቡለት ሄሮድስ ደግሞ መንግስቴን ሊቀማኝ ነው በማለት አሳደደው፡፡ በአንፃሩ ደግሞ አይሁድ ይጠብቁት የነበረው መሲህ በኃይሉ ጽናት ቅኝ ገዢዎቻቸውን ሮማውያንን አባርሮ ሀገራቸውን ፍልስጤምን ነፃ የሚያወጣ የዳዊትን መንግስት በኢየሩሳሌም በመመለስለነርሱ ምድራዊ ስልጣንን የሚያጎናጽፍ መሲህ ይጠብቁ ነበር፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣው የሰውን ልጅ ወደቀደመ ክብሩ ይመልስ ዘንድ በኃጢአት ምክንያት አጥፍቶ የነበረውን ሰማያዊ መንግስት እንደገና ያጎናጽፍ ዘንድ ነውና አይሁድ ጌታን በአደባባይ ከሰው በጲላቶስ ፊት ለፍርድ አቆሙት፡፡ የሐሰት ምስክሮችም አቁመው እንዲሞት ፈረዱበት፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “አንተ ጴጥሮስ ነህ በዚህችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም” ማቴ 16÷18 በማለት እንደገለፀው አማናዊቷን ቤተ ክርስቲያን በዚሁ በዕለት ዓርብ በደሙ መሠረታት፡፡ ሐዋ 20÷28
በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኃላ ለ፵ ቀናት እየተገለጠ ለደቀ መዛሙርቱ ሲያስተምራቸው ምስጢር ሲገልጥላቸውና ሲያጽናናቸው ከቆየ በኃላ በ፵ ኛው ቀን በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ በ፲ ኛው ቀን (ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በ፶ ኛው ቀን) በኢየሩሳሌም ከተማ በጽርሐጽዮን በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ተሰብስበው ሲጸልዩ ለደቀ መዝሙርቱ መንፈስ ቅዱስ ወረደላቸው፡፡ በእሳት ላንቃ አምሳል አምሳል በእያንዳንዳቸው ራስ ላይም ይታይ ነበር፡፡ ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስ ከተቀበሉ በኃላ ፍሩህን የነበሩት ጥቡዓን ደካሞች የነበሩት ብርቱዎች ሆነው በመንፈስ ታድሰው የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ በዚሁ ዕለት ጀመሩ፡፡ ሃምሳኛው ዕለት አይሁድ የእሸት በዓል የሚያከብሩበት ቀን ነበርና ከሚኖሩበት ሀገር ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተሰብስበው ነበርና ሐዋርያት ቋንቋ ተገልጦላቸው በአደባባይ ለእያንዳንዱ ሰው በየተወለደበት ቋንቋ የክርስቶስን ወንጌል ሰበኩ፡፡ በዚሁ ዕለት ብቻ በቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት ፫ሺ አይሁድ አምነው በመጠመቅ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ተቀላቀሉ፡፡ ስለዚህም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይህችን ዕለት የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን ቅዳሴ ቤት” በማለት ሰይመዋታል፡፡
3.2 ቤተክርስቲያን በዘመነ ሐዋርያት
ሐዋርያት የሚለዉቃል የሐዋርያ ብዙ ቁጥር ሲሆን ሐዋርያ ማለትም ሖረ ሔደ ካለዉ የግዕዝ ግስ የወጣ ነዉ፡፡ ትርጉሙም የተላከ፣ ሂያጅ፤ ልዑክ ማለት ነዉ፡፡ ወንጌለ መንግስትን፣ ድኀነት ዓለምን ለመላዉ ዓለም ሊያዉጁ ወይንም ሊያበስሩ ተልከዋልና፡፡ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በ30 ዘመኑ በማየ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ተጠምቆ 40 ቀንና 40 ሌሊት በገዳመ ቆሮንቶስ ከጾመና ከጸለየ በኃላ የማስተማር ስራዉን ሲጀመር አስቀድሞ ያደረገዉ ነገር ቢኖርቃሉን ሰምተው፣ ተአምራቱን አይተው በዓለም ዞረው ወንጌልን የሚሰብኩ ደቀመዛሙርቱን መምረጥ ነበር፡፡ እነዚህ ደቀመዛሙርቱም ሐዋርያት ተብለው ይጠራሉ፡፡ ቅዱስ ማርቆስ በወንጌሉ እንደ ገለጠው አስቀድሞ ከእርሱ ጋር እንዲኖሩከጠራቸው በኋላ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የገለጠውን ድንቅ ሥራ አምላክ ሰው ሆኖ ያደረገውን ተአምራት ለአለም ድህነት ያደረገውን ስራ ዞረው እንዲሰብኩ ነገራቸው፡፡ ማር3÷13 ጌታችንሐዋርያትንከድሆችም ከሀብታሞችም መርጦአል፡፡ እነቅዱስ ጴጥሮስን የመሰለ ድሀ ዓሳ አጥማጆችን ሲጠራእነ ቅዱስ ማቴዎስን የመሰለበቀረጥ ብር የከበሩትንም አልተዋቸውም፡፡ ሁሉም በእግዚአብሔር ዘንድ እኩል ናቸውና፡፡ ሁሉም ደግሞ ያላቸውንትተዉ ተከትለውታል፡፡ ማቴ 4÷20 ማቴ 9÷9 ከተማሩትም ከማያምኑትም ወገን መርጧል፡፡ ዮሐንስና ያዕቆብን ጌታ የጠራቸዉ ከአባታቸዉጋር ዓሣ ሲያጠምዱ ነዉ፡፡ ሌላ ትምህርትአልነበራቸዉም፡፡ ነገር ግን አልናቅናቸዉም፡፡ ምሁር ኦሪት የነበረዉን ናትናኤልንጠርቶታል አልተወዉም፡፡ የቀናተኞች አይሁድ ወገን በመሆኑ በዚያን ዘመን ሮማዉያንን ለማስወጣት ዉስጥ ዉስጡን በምድረ ፍላስጤም ይካሄድ የነበረዉ ግርግር ስምዖንን አዉጥቶ የሰላምና የፀጥታ ወደብ ባለቤት ወደ ሆነዉ ወደ እሱ ጠርቶታል፡፡ ቤተ እስራኤልስ ትመሰረት 12ቱ አበዉ እየተባሉ በሚጠሩት ከያዕቆብ አብራክ በተከፈሉ አሥራ ሁለት ነገድ አባቶች ነበር አሁንም በክርስቶስ ፍቃድ የእስራኤል ዘነፍስ ማህበር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን 12ቱ ሐዋርያት ተመሰረተች፡፡
ሐዋርያት እስከ መጨረሻዉ በመፅናት ለክርስቶስ ምስክር ለመሆን የበቁባቸዉ ዋናዋና ምክንያቶች፡
1. በዓይናቸው አይተውታልና
2. በእጃቸው ዳስሰውታል
3. ትምህርቱን በጆሮአቸው ሰምተውታልና /ዮሐ.1÷2/
4. በእርሱ ተልከዋልና /ማቴ.10÷1-4/
5. ከትንሣኤው በኋላም አይተውታልና /ዮሐ 21/
6. በስሙ ተአምራት ሲፈጹሙ ኖረዋልና /2ቆሮ. 12÷12/
ከዚህ በፊት በሌዋውያን ዘር ይወርድ የነበረውን የብሉይ ኪዳን ሥልጣነ ክህነት በአዲስ በመተካት ለእነርሱ ሰጣቸው፡፡ ዮሐ20÷22 እነሱም ጌታችን እንዳስተማራቸውና ቃል ኪዳን እንደገባላቸው ለተከታዮቻቸው ይህንን ሥልጣን በአንብሮተ ዕድና በንፋሐት በመሾም አስተላለፉ፡፡ ማቴ 28÷20 የሐዋ 9÷20 በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የተዋጀችውን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን በስብከታቸው በሰጣቸውሥልጣን ባደላቸውም ጸጋ ጠብቀው አቆዩአት፡፡ የመጀመሪያ ሥራቸውንም በቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት 5ሺ ምዕመናንን ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በማስገባት በይፋጀመሩ፡፡ ከዚህም ዓለምንዕጣ በዕጣ ተካፍለው ተዘዋውረው አስተማሩ፡፡ ወንጌልን ሰብከው ቤተ ክርስቲያንን አነፁ፡፡ አምልኮ ጣኦትን አጠፉ፡፡ ርኩሳት አጋንንትን አሳደዱ፡፡ በመስቀል እርፍ አርሰው ንጹህ ዘር ወንጌልን ዘርተው በደማቸው አተሙ፡፡ ለአስተማሩት ሕዝብ ለእምነቱ ማጽኛ የሚሆኑ መልዕክታትን ጻፉ፡፡ ሥርአተ ቤተ ክርስቲያንን ደነገጉ ከጌታ የተማሩትን ያዩትንና የሰሙትን ለተከታዮቻቸው በቃልም በኑሮም በመጻሕፍትም አውርሰው በተጋድሎ አረፉ፡፡
3.3 የአስራሁለቱ ሐዋርያትታሪክ
አሥራሁለቱ ሐዋርያት ትውልዳቸው ከአሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤልነው፡፡ ጴጥሮስና ወንድሙእንድርያስ አባታቸው ከነገደ ሮቤል ሲሆን እናታቸው ደግሞ ከነገደ ስምዖንናት፡፡ ያዕቆብና ወንድሙና ዮሐንስ አባታቸው ከነገደ ይሁዳ ሲሆን እናታቸው ደግሞ ከነገደ ሌዊ ናት፡፡ ፊሊጶስ ከነገደ ዛብሎን፣ በርተሎሜዎስ ከነገደ ንፍታሌም፣ ቶማስ ከነገደ አሴር፣ ማቴዎስ ከነገደ ይሳኮር፣ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ ከነገደጋድ፣ ስምዖን ቀነናዊ ከነገደ ብንያም፣ ታዴዎስ የተባለው ልብድዮስ ከነገደ ዮሴፍ፣ በይሁዳ ምትክ የገባው ማትያስ ከነገደ ዳን ናቸው፡፡
3.3.1 ሐዋርያውቅዱስጴጥሮስ
ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው በቤተሳይዳነው፡፡ የአባቱስም ዮና ይባላል ጌታን ከመከተሉ በፊት ከአምስት አመት ጀምሮ ያደገው በቅፍረናሆም ከተማ ሲሆን በጎልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባህር ዓሳ አጥማጅ ነበር፡፡ ማር1÷16 ለደቀመዝሙርነት ሲመረጥ ዕድሜው 55ዓመት እንደ ነበረ ይነገራል፡፡ የመጀመሪያ ስሙ ስምዖን ሲሆን ጌታችን ጴጥሮስ ብሎታል፡፡ በላቲንቋንቋ ዐለት በአረማይክ ኬፋበግዕዝኰኩሕ ማለትነው፡፡ የመንግስተ ሠማያት ቁልፍ ተሰጥቶታል፡፡ የቤተ ክርስቲያን መዛግብት ስለቅዱስ ጴጥሮስ መልክና ቁመት ሲገልፁ ፊቱ ሰፋ ያለ ሲሆንሪዛምና መካከለኛ ቁመት የነበረው ራሰ በራሰው በማናቸውም ነገር ፈጣንና ቀልጣፋ እነደ ነበርይነገርለታል፡፡ መንፈስቅዱስን እንደተቀበለበአንድቀን ስብከት አምስት ሺሰዎችን አሳምኖ አጥምቋቸዋል፡፡ቅዱስ ጴጥሮስበፍልስጥኤም፣ በልዳ፣ በኢዮጴ፣ በቂሳሪያ፣ በሶሪያ፣ በጳንጦን፣ በገላትያ፣ በቀጰዶቂያ፣ በቢታኒያ በሮሜና በተለያዩ ሀገሮች እየተዘዋወረ አስተምሮ አሳምኗል፡፡ሐዋ2÷41 ከአህዛብ ወገን የነበረውን ቆርኔሌዎስንም ከነቤተሰቡ አጥምቋል፡፡ ሐዋ10÷48፡፡ በጥብርያዶስ ባሕር ጌታ እዳዳ ነው ማቴ14÷22 ማልኮስን በሰይፍ ጆሮውን እንደ ቆረጠ ዮሐ18÷10 ጌታ በአይሁድ እጅ ተይዞ ሳለ የገባውን ቃል አጥፎ ሦስት ጊዜ ጌታን አላውቀውም ብሎ እንደካደ ማቴ 26÷69 በኋላ ግን በንስሐ በመመለሱ ጌታ ግልገሎቼን አሰማራ ጠቦቶቼን ጠብቅ በጎቼን አሰማራ በማለት አደራ እንደሰጠው በወንጌል ተገልጿል ዮሐ 21÷15 ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም ንጉሰ ነገስት ኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግስት በክርስቲያኖች ላይ በተነሳው ስደትና መከራ በመስቀል ተሰቅሎ በሰማዕትነት አረፈ፡፡ በአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው የቤተ ክርስቲያን ፀሐፊ ቅዱስ ጴጥሮስ በቫቲካን ኮረብታ ጳውሎስ ደግሞ በሮም በአስቲያ መንገድ መቀበራቸውን መስክሯል፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያኛችንም የእነዚህን ታላላቅ የቤተክርስቲያን መሠረቶች የሆኑ ቅዱሳን አባቶች የዕረፍታቸውን መታሰቢያ በዓል በየዓመቱ ሐምሌ 5ቀን ታከብራለች፡፡
3.3.2 ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ
የቅዱስ ዮሐንስ ሀገሩ ገሊላ አውራጃ ሲሆን ከወንድሙ ከቅዱስ ያዕቆብና ከአባቱ ከዘብዴዎስ ጋር ዓሣ ያጠምድ ነበር፡፡ ማር1÷19 ጌታ በመስቀል ላይ ሳለ እመቤታችንን እንዲያገለግላት አደራ የተሰጠው ለዮሐንስ ነው፡፡ ዮሐ19÷26፡፡ ጌታ ይወደው የነበረው ዮሐንስ በፍልስጥኤምና በሌሎችም ቦታዎች ክርስትና እንዲስፋፋ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር በመተባበር አስተምሯል፡፡ ሐዋ4÷1-22፣ 8÷14፡፡ ከኢየሩሳሌም ወደ ኤፌሶን በመሄድ በታናሽዋ እስያ የነበሩበትን አብያተ ክርስቲያናት በማስተማር ሲያገለግል ቆይቶ በድምጥያኖስ ዘመነ መንግስት ከ81-96 ዓ.ም ወደ ደሴተ ፍጥሞ ተሰዶ በግዞት ሳለ ራዕየ ዮሐንስን ጽፏል፡፡ ጌታ በተሰቀለበት ዘመን የሮማ ንጉስ የነበረው ጢባሪዮስ ቄሳር (ከ14-31ዓም) ልጁ በሽተኛ ስለ ነበረ ወስደው በጌታ መቃብር ላይ ሲያኖሩት ተፈወሰ፡፡ ለጌታ ያለውን ፍቅር ለመግለጥ የጌታን ስዕል የሚስልለት ሲፈልግ ከዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ጋር ተገናኘና ልክ በዕለተ ዓርብ እንዳየው አድርጎ ሥሎ ሰጥቶታል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሰፊ ቦታ የሚሰጠው አባት ነው፡፡
3.3.3 ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ (ወልደ ዘብዴዎስ)
ቅዱስ ያዕቆብ የዮሐንስ ወንድም ሲሆን የመጀመሪያው ስራው ከአባቱ ጋር ዓሳ ማጥመድ ነበር፡፡ ማር1-19 ያዕቆብ በኢየሩሳሌም ውስጥ በተመሰረተችው ቤተ-ክርስቲያን መሪ ሆኖ በማስተማር ከፍ ያለ አገልግሎትን አበርክቷል፡፡ በእስፔን ሀገርም እንደሰበከ የቤተክርስቲያን የታሪክ መዛግብት ይነገራሉ፡፡ የክርስትናን ትምህርት በስፋት በማስተማሩ በአይሁድ ዘንድ እንደ ወንጀለኛይቆጠር ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ሄሮድስ አግሪጳ አይሁድን ለማስደሰት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በ44 ዓ.ም አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ የሐዋ12÷2 ቅዱስ ያዕቆብ የኖረውም ያረፈውም በኢየሩሳሌም ከተማ ነው፡፡ቅዱስ ያዕቆብ ከ12ቱ ሐዋርያት መካከል መጀመሪያ የሰማዕትነትን አክሊል የተቀዳጀ ሲሆን ሰማዕትነቱ በሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ የተጻፈለት ብቸኛ ሐዋርያ ነው፡፡እነዚህ እስካሁን ከላይ ያየናቸው ሦስት ሐዋርያት ማለትም ጴጥሮስ ዮሐንስና ያዕቆብ አዕማደ ሐዋርያት ይባላሉ፡፡
3.3.4 ሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ
ቅዱስ እንድርያስ የቅዱስ ጴጥሮስ ወንድም ሲሆን ትውልዱም በቤተ ሳይዳ ነው፡፡በዓሳ ማጥመድ ተግባር ላይ ሳለ በጌታ ቃል በመጀመሪያ የተጠራ ሐዋርያ ነው፡፡ ዮሐ1÷35-45 ጌታን ከመከተሉ በፊት የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ነበር፡፡ ዮሐ1÷41 በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ሲማር ለቆየው ሕዝብ ቅዱስ እንድርያስ አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሳ የያዘውን ወጣት አቅርቦ አስባርኮታል፡፡ ጌታም በዚያን ቀን 5ሺ ሕዝብ በበረከት አጥግቧል፡፡ዮሐ6÷6 ቅዱስ እንድርያስ መጀመሪያ የስብከት ስራውን በፍልስጤም ጀመረ፡፡የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊ የነበረው አውሳብዮስ እንደገለጠው እንድርያስ በሩሲያ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ቀጥሎም በቢታንያ፣ በገላቲያ፣ በሩማንያ፣ በሜቄዶንያ፣ በታናሽ እስያና በግሪክ አገር አስተምሯል፡፡ በቁስጥንጥንያ ቤተ ክርስቲያን የመሰረተና የቁስጥንጥንያ የመጀመሪያ ሊቀ ጳጳስ መሆኑ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይነገራል፡፡ በመጨረሻም ግሪክ ውስጥ ምትራ በምትባለዋ ሀገር ሲያስተምር በጣዖት አምላኪዎች እጅ የሚመስል ቅርጽ ባለው መስቀል ተሰቅሎ በድንጋይ ተወግሮ ታኅሣስ 4 ቀን በ80ዓ.ም በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡
3.3.5 ሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጶስ
ቅዱስ ፊሊጶስ ሀገሩ ቤተ-ሳይዳ ነው፡፡ ዮሐ1-14 ጌታ ተከተለኝ ባለው ጊዜ ወዲያውኑ ጥሪውን በመቀበል ጌታን ከመከተሉም በተጨማሪ ናትናኤልን ወደ ጌታ ያቀረበ (የጠራ) እርሱ ነው፡፡ዮሐ1-46 ጌታችንን ለማየት የፈለጉትን ከአሕዛብ ወገን የነበሩት ግሪኮች ለመጀመሪያ ጊዜ ቀርበው የተማሩት በፊልጶስና በእንድሪያስ አቅራቢነት ነበር፡፡ ዮሐ 12÷20፡፡ፊልጶስ “አብን አሳየንና ይበቃናል”ብሎ ኢየሱስ ክርስቶስን በመጠየቁ ለክርስትና እምነት መሰረት የሆነውን የሚስጢረ ሥላሴን ትምህርት“እኔን ያየ አብን አየ…እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን…” በማለት አስረድቶታል፡፡ ዮሐ14÷8 ሐዋርያው ወንጌልን በታናሽ እስያ ውስጥ በምትገኘው በፍርግያ አስተምሯል፡፡በመጨረሻም በታናሽ እስያ ሲያስተምር በተቃዋሚዎች እጅ ተሰቅሎ ዐርፏል፡፡
3.3.6 ሐዋርያ ውቅዱስ ቶማስ
ሐዋርያው ቶማስ በፋርስና በሕንድ አስተምሯል፡፡ሕንድ የደረሰው በ46 ዓም ገደማ ነው፡፡ የሕንድ ንጉስ የነበረው ሳንዶ ፖረስ በኢየሩሳሌም እንደነበረው የሰሎሞን ቤተ መንግስት ለማሰራት ሙያ ያለው ሰው ሲያፈላልግ ቅዱስ ቶማስ እሠራልሃለሁ በማለት ገንዘቡን ተቀብሎ ለተራቡና ለታረዙ ለበሽተኞች መጠለያ ላጡ ችግረኞች ማደል ጀመረ፡፡ ንጉሡም ቤተ መንግሥቱን እንዳልሰራለት ባወቀ ጊዜ ተናዶ ወደ ወህኒ አወረደው በዚያች ሌሊት ለንጉሡ ወንድም መላዕክት በራዕይ ቶማስ ምክንያት ሆኖት በሰማይ ያዘጋጀለትን ቤተመንግስት አሳዩት፡፡ ንጉሱም ይህን ሲሰማ ተደስቶ ቶማስን ከወህኒ አወጣውና ያለውን ሁሉ ገንዘብ ሰጥቶት አሰረ ፍኖቱን በመከተል የወንጌል አገልጋይ እንደሆነ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይወሳል፡፡
ጌታ ከሙታን እንደተነሣ ለሐዋርያት በተገለጠበት ጊዜ ቶማስ ስላልነበረ ከሞት መነሳቱን ሐዋርያት ሲነግሩት ሳላይ አላምንም አላቸው፡፡ጌታም ሁሉም ባሉበት እንደገና ተገልጦ ቶማስ በጣቱ የጌታን የተወጋ ጎኑን የተቸነከረውን እጅና እግሩን ዳስሶ አምኗል፡፡ “ጌታዬ አምላኬ”ብሎም መስክሯል፡፡ ዮሐ 20-19
መምለክያነ ጣዖት በ66ዓ.ም የቅዱስ ቶማስን ቆዳውን ገፈው ስልቻ በመሥራት በሰውነቱ ላይ ጨው ነስንሰው በቆዳው አሸዋ በመሙላት አሸክመው በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደሉት ታሪክ ይመሰክራል፡፡
3.3.7 ሐዋርያው ቅዱስ በርተሎሜዎስ
ሐዋርያው ቅዱስ በርተሎሜዎስ ስሙ በሐዲስ ኪዳን ላይ የተገለጠው በሐዋርያት ዝርዝር ላይ ብቻ ሲሆን ታሪኩ በሐዲስ ኪዳን ተጽፎ አይገኝም፡፡ ትውልዱ ከነገደ ንፍታሌም ነው፡፡ጌታን ከተከተለ በኋላ የወንጌልን ትምህርት በዐረብ፣ በሕንድ፣ በአርመንያና እንዲሁም በአካባቢ ዋአ ስተምሯል፡፡የአርመንን መንበር ያቋቋመው ቅዱስ በርተሎሜዎስ ነው፡፡ በገድለ ሐዋርያት ተጽፎ እንደምናገኘው ቅዱስ በርተሎሜዎስ በሐዋርያት ዕጣ የደረሰው አልዋህ በተባለ ሀገር ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥርስ በርተሎሜዎስን ለማድረስ ሲል አብረው ወደ አልዋህ ተጓዙ ፡፡ ተማክረው ነበርና የተጓዙት አንድ ነጋዴ ሲመጣ ቅዱስ ጴጥሮስ “ይህንን ባሪያዬን በሀገረ አልዋህ ልሸጠው ፈልጌያለሁ እባክህ ወደ ሀገርህ ውሰድልኝ” ሲል ጠየቀው ያም ነጋዴ “ለቤቴ አገልጋይ የሚሆን ሰው አጥቼ እኖር ነበር”፡፡ “ለመሆኑ ስራው ምንድን ነው”፡፡ብሎ ጠየቀው ቅዱስ ጴጥሮስም ቀለል አድርጎ “ወይን ጠባቂ ነው” አለው፡፡ ነጋዴውም ብዙ ወይንስ ለነበረው በ30 አስታቴር ገዛው፡፡ ቅዱስ በርተሎሜዎስ በአርመንያ ሲኖር አንድ ቀን የወይን ባለጸጋው እባብ ነድፎት ለሞት ስላበቃው ወዳጅ ዘመዶቹ ለለቅሶ ተሰብስበው ሳሉ በርተሎሜዎስ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ ከሞት አስነሳው፡፡ በዚህም ተአምር ሕዝቡ መኳንንቱና መሳፍንቱ ሁሉ ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር ተመለሱ፡፡ በተአምራቱና በትምህርቱ ብዙ ክርስቲያኖችን በማፍራት በቅናት ሰዎች ተነስተውበት መስከረም አንድ ቀን አሸዋ በተሞላ ከረጢት ውስጥ ከተው ከነ ሕይወቱ ባሕር ውስጥ ጣሉት፡፡ በዚያም ዐረፈ በነጋውም ክርስቲያኖች ምዕመናን ከባሕር አውጥተው እንደቀበሩት የቤተክርስቲያን የታሪክ መዛግብት ይናገራሉ፡፡
3.3.8 ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ (ሌዊ)
ቅዱስ ማቴዎስ የመጀመሪያው ስሙሌዊ ነው፡፡ ማር2- 14 ማቴዎስ የሚለውን ስም ያወጣለት ጌታነው፡፡ ማቴዎስ የቀድሞ ሥራው ቀራጭ ነበር፡፡ ማቴ9-9 የቀረጥ ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ጌታ ጠጋ ብሎ “ተከተለኝ ” አለው፡፡ ወዲያው በቤቱ ታላቅ ግብዣ ለጌታ አድርጎ ጓደኞቹ የነበሩትን ቀራጮችን ወደ ጌታ አቅርቦ ካገናኛቸው በኋላ ሁሉንም ትቶ ተከተለው፡፡ ሉቃ 5-26 በዚህም አንዳንዶች ቅዱስ ማቴዎስን የቁም ተዝካሩን አውጥቶ ጌታን የተከተለ ሐዋርያ ይሉታል፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ ለስብከት ሲሰማራ በዕጣ የደረሰችው ሀገር ምድረ ፍልስጥኤም ስትሆን ቀጥሎ በኢትዮጵያ በፋርስ በባቢሎን አካባቢ እንደሰበከ ይናገራል፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ የአይሁድና የአረማውያንን ትምህርት እየተቋቋመ ድውዩን ሲፈውስ አጋንንትን ሲያወጣ ልዩ ልዩ ተአምራትን ሲያደርግ ዝናው በከተማ ሁሉ በመዳረሱ በዚህ የተናደዱ መኳንንት የሞት ፍርድ ፈረዱበት ጥቅምት 12ቀን አንገቱን በሰይፍ ተሰይፎ አርፏል፡፡
3.3.9 ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ /ወልደ እልፍዮስ/
የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ ጸሎት ወዳድ ስለነበር ለብዙ ሰዓታት መቆም ስለሚያበዛ እግሩ ያብጥበት ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳ እንደ ሌሎች ሐዋርያት ተዘዋውሮ ማስተማር ባለመቻሉ የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ በመሆን ተሾመ፡፡ በ50 ዓም አካባቢ በኢየሩሳሌም የተደረገውን ሲኖዶስ በሊቀ-መንበርነት የመራው እርሱ ነው፡፡ በኢየሩሳሌም ከተማ ትኖር ለነበረችው ቴርዮብስጣ ለተባለች ደግሴት ልጅ ስላልነበራት ያዕቆብ “አይዞሽ እመኝ እንጂ ይደረግልሻል” በማለት አጽናንቶ በዓመቱ ወንድ ልጅ ወልዳለች፡፡ በዚህ ጊዜ አይሁድና በዘመኑ የነበረው ሊቀ ካህናት ሐናንያ ክርስቲያኖች ቁጥራቸው እንዳይጨምር ያዕቆብን አሰሩት፡፡
ሊቀ ካህናቱ አይሁድን ሰብስቦ ያዕቆብ ክርስቶስን ክዶ እንዲያስተምር ቢጠይቀው ቅዱስ ያዕቆብ ጌታን በመካድ ፈንታ የኢየሱስን የማዳን ስራ ጌትነቱንና አምላክነቱን መስክሯል በዚህ የተናደዱት የአይሁድ አለቆች ያዕቆብን ከቤተ-መቅደስ ጫፍ ወደ ምድር ወረወሩት፡፡ ከዚያም ከሥር ያሉት አይሁድ በድንጋይ ወግረው የካቲት10 ቀን 62ዓ.ም ገደሉት፡፡
3.3.10 ሐዋርያው ናትናኤል
የተወለደውናዝሬት በምትገኘውበቃናዘገሊላ ነው፡፡ዮሐ1÷2የመጀመሪያ ስሙስምዖንሲሆን ናትናኤልብሎየጠራው ጌታነው፡፡የትውልድዘመኑጌታችንበተወለደበት ዘመንአካባቢ እንደሆነ ይነገራል፡፡ምክንያቱምሄሮድስየቤተልሄም ህፃናትንበሚያስፈጅበትጊዜእናቱ ከበለስ ሥርደብቃ አትርፋዋለችና፡፡“ጌታ ፊሊጶስ ሳይተራህ ከበለስሥርሳለህአውቅሃለሁ”ያለው ለዚህነው፡፡ወደጌታ የጠራውፊሊጶስሲሆን የኦሪትምሁርነበር፡፡ መጻሕፍትንምበማወቁ“ከናዝሬትመልካምነገር ይወጣልን” በማለትየነቢያትን ቃል ተናገረ፡፡ዮሐ1÷44
ናትናኤል ለሐዋርያነትከመጠራቱበፊት ለሕገኦሪት ቀናተኛ ስለነበረቀናተኛተባለ፡፡ማር3÷19ሐዋረያውናትናኤል/ስምዖን/ወንጌልንበሶሪያ፣ በባቢሎን፣ በግብፅና ሊቢያእየተዘዋወረአስተምሮአል፡፡ ማቴ10÷4በመጨረሻምበግብጽ ሲያስተምር ሕዝቡበትምህርቱአምነውበመብዛታቸው አረማውያኑስለቀኑበት ለግብፅንጉስእንድርያኖስከስሰውበሠራዊት በማስያዝበንጉሱ ትዕዛዝሐምሌ 10ቀን በሰይፍአስገደሉት፡፡
3.3.11 ሐዋርያው ታዴዎስ /ልብድዮስ/
የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ በመባል ይታወቃል፡፡ ሐዋ1÷13፤ ሉቃ6÷16 ታዴዎሰ ልብድዮስ እየተባለም ይጠራል፡፡ ማቴ10÷4 የሐዋርያው ታዴዎስ ሀገረ ስብከት ሶርያ ሲሆን በተጨማሪም በፍልስጥኤም፣ በአርመን ናበፋርስ አስተምሯል፡፡ ሶርያ ውስጥ ሲያስተምር “ባለጸጋ መንግስተ-ሰማያት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብታልፍ ይቀላል፡፡” እያለ ሲያስተምር አንዱ እስኪ የተናገርከውን በተግባር አሳየኝ በማለት ጠየቀው፡፡ ታዴዎስ ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ ለአመነ ሁሉ ይቻላል” በማለት ግመሉን በመርፌ ቀዳዳ አሹልኮ አሳየው፡፡ በዚህም የተነሳ በአካባቢው የነበሩ ትምህርቱን የሰሙ ተአምራቱን ያዩ ሁሉ እንዳመኑና እንደ ተጠመቁ ብዙዎቹም ክርስቲያኖች እንደሆኑ የቤተ-ክርስቲያን ታሪክ ይመሰክራል፡፡ ሐዋርያው ታዴዎስ ተአምራትን ሲያደርግና ሲያስተምር ቆይቶ ሐምሌ2 ቀን በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡
3.3.12 ሐዋርያው ማትያስ
ሐዋርያው ማትያስ ጌታን በሸጠው በአስቆሮቱ ይሁዳ ምትክ የተሾመ ነው፡፡ ሐዋ1÷15 በቤተክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊነቱ የታወቀው አውሳብዮስ ቅዱስ ማትያስ ከሰባው አርድዕት ወገን እንደነበረ ጽፏል፡፡ ማትያስ ለሐዋርያነት እንዲመረጥና ዮስጦስ በርስያ ከተባለው ከዮሴፍ ጋር ዕጣ እንዲጣጣል ሐሳብ ያቀረበው ቅዱስ ጴጥሮስ እንደተናገረው ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስካረገበት ቀን ድረስ ከሐዋርያት መካከልም በገባበትና በወጣበትም ዘመን ሁሉ ማትያስ ከሐዋርያትጋር ነበረ፡፡ ሐዋ 1÷21 ኪዚህ በኋላ ቅዱስ ማትያስ ወደ ቀጰዶቅያና ወደ ካስፒንያ ባሕር አካባቢ የክረስትና ሃይማኖት እንደመሠረተ አንድ የግሪክ ትውፊት ይነግረናል፡፡ በዚያም ሳለ ከአሕዛብና ከጣዖት አምላኪዎች ብዙ ችግርና መከራ ደርሶበታል፡፡ በዚያው አገር ሰማዕትነት ተቀብሎ ሞቷል፡፡
3.3.13 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
ቅዱስ ጳውሎስ የስሙ ትርጓሜ ብርሃን ማለት ነው፡፡ ሰርግዮስ ጳውሎስ የተባለ ሀገረ ገዥ የገዛ ስሙን ሰጥቶት ነው የቀደመ ስሙ ሳውል ነበር።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ዘሩ ከዕብራውያን ከብንያም ነገድ ሲሆን የተወለደውም በጠርሴስ ከተማ ነው፡፡ ድንኳን መስፋትን የተማረው በዚያ ነው። የሐዋ ፲፫፥፫ ጠርሴስ በንግድም የታወቀች የኪልቂያ ዋና ከተማ ናት፡፡ ከተማዋ እስከ አምስት መቶ ሺ የሚገመት ከየ ሀገሩ የተሰባሰቡ ሕዝቦች ነበሩባት፡፡ ሮማውያን በሥራቸው ለሚተዳደሩት ሕዝቦች ሮማዊ ዜግነት ይሰጡ ስለነበር የቅዱስ ጳውሎስ አባት በዜግነት ሮማዊ ነበር፡፡ ይህም ለቅዱስ ጳውሎስ ተላልፎለታል፡፡ አባቱ የሮም ዜግነት ይኑረው እንጂ፡- ከብንያም ወገን የሆነ ፈሪሳዊ ነበረ። የሐዋ ፳፫፥፮ በፊልጵስዩስ መልእክቱ፡-«በስምንተኛው ቀን የተገረዝሁ ከእስራኤል ትውልድ፥ ከብንያም ወገን፥ ከዕብራውያን ዕብራዊነኝ፤ስለሕግ ብትጠይቁኝ ፈሪሳዊ ነበርሁ፤ በሕግ ስለሚገኝ ጽድቅ ያለነቀፋ ነበርሁ።»ያለው ለዚህ ነው። ፊል፫፥፭ ከታላቁ መምህር ከገማልያል እግር ስር ሆኖ ሕገ ኦሪትንና የአይሁድን ወግ ጠንቅቆ ተምሯል። የሐዋ ፳፪፥፫
ቅዱስ ጳውሎስ በ15 ዓመት ዕድሜው ወደ ትውልድ ሀገሩ በመመለስ በኢየሩሳሌም ከነበረው የታወቀው የገማልያል ትምህርት ቤት ገባ፡፡ በዚያም የአይሁድን ሕግና ሥርዓት እየተማረ እስከ 30 ዓመቱ ቆየ፡፡ ገማልያል ፈሪሳዊ ስለነበር ጳውሎስም ይህን ተቀብሎታል፡፡ በ30 ዓመቱ የአይሁድ ሸንጐ (ሳንኽርይን) አካል ሆኖ ተቆጠረ፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ጥሪ
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ዘመን ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ስለነበረ ሁኔታ ዎቹን ሁሉ ያውቃል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በአይሁድ ሸንጎ አባልነት ለሁለት ዓመታት በሠራበት ወቅት ለኦሪታዊ እምነቱ ቀናተኛ ፈሪሳዊ በመሆኑ ክርስቲያኖችን በማናቸውም አጋጣሚ ይቃወም ነበር፡፡ እንዲያውም ሊቀዲያቆናት እስጢፋኖስ በማስተማሩ ምክንያት ተከሶ ለአይሁድ ሸንጎ በቀረበ ጊዜ የተከራከረው እርሱ ነበር፡፡ በድንጋይ ተወግሮ በሰማዕትነት ሲያርፍም የወጋሪዎችን ልብስ ይጠብቅ የነበረው እርሱ ነው፡፡ ቅዱስ አውግስጢኖስ ‹በእስጢፋኖስ ጸሎት ቤተ-ክርስቲያን የጠፋውን ጳውሎስን አገኘች፡፡› በማለት ተናግሯል፡፡ በእስጢፋኖስ ሞት የተበተኑ ክርስቲያኖች ብዙዎችን ሰዎች በማጥመቅ ክርስቲያኖች እያደረጉ መሆኑን ጳውሎስ ሲሰማ ክርስቲያን የሆኑትን ወንዶችንም ሴቶችንም ለማሰር የሚያስችለው ፈቃድ ወሰደ፡፡ በ32 ዓመት ዕድሜው ከኢየሩሳሌም 223 ኪ.ሜ ርቀት በስተሰሜን በኩል በምትገኘው የደማስቆ ከተማ ብዙ ክርስቲያኖች መኖራቸውን ሲሰማ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቀርቦ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የሚያስችለውን የፈቃድ ደብዳቤ አገኘ፡፡ ከዚህ በኋላ ጭፍሮችን አስከትሎ ወደ ደማስቆ አመራ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ከተማዋ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረው ነበር ከሰማይ የወረደው ብርሃን አካባቢውን ያለበሰውና ‹ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ የሚለውን ድምፅ የሰማው፡፡ሐዋርያው ጳውሎስም ‹ጌታ ሆይ ማን ነህ ብሎ ጠየቀ፡፡ ‹አንተ የምታሳድደኝ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ፡፡ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስበኻል› ሲል መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተናገረው፡፡ ያንጊዜም በወደቀበት ሆኖ እየተንቀጠቀጠ ‹ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ ሲል ጠየቀ፡፡ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ወደ ደማስቆ እንዲገባ ተነገረው፡፡ የሐዋ9.1
ወደ ደማስቆ ገብቶ ሦስት ቀን ምግብ ሳይበላ ውሃ ሳይጠጣ ቆይቶ ቁጥሩ ከሰባ ሁለቱ አርድዕት የሆነው ሐናንያ አጠመቀው፡፡ በተጠመቀም ጊዜ ዓይኑ በራለት ምስጢርም ተገለጠለት መንፈስ ቅዱስም አደረበት፡፡
ከተመለሰ በኋላ
ለ3 ዓመታት በዓረቢያ በረሃ ከቆየ በኋላ ወደ ደማስቆ ከተማ ተመለሰ፡፡ በዚያም በነበሩ አይሁድ መካከል በፊት ያሳድደው የነበረውን ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ጀመረ፡፡ ከዚያ በፊት በፈሪሳዊነቱ ለአይሁድ ሕግ በነበረው ቅንዓት የሚታወቀው ጳውሎስ ዛሬ ወንጌል ሲሰብክ በማየታቸው አይሁድ ተነሡበት፡፡ በዚህም የተነሣ የደማስቆ ክርስቲያኖች በቅርጫት አውርደው ወደ ኢየሩሳሌም ላኩት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ የገጠመው ሁለት ችግር ነበር፡፡ እነርሱም፡-
1. አይሁድ ጳውሎስን እንደሚያውቁት እና እንደለመዱት ሆኖ ስላላገኙት ሊገድሉት ተነሡ፡፡
2. ክርስቲያኖች የቅዱስ ጳውሎስን መመለስ ሊያምኑ አልቻሉም፡፡ በመጨረሻ ግን በርናባስ ወደ ሐዋርያት ዘንድ ወስዶ የጳውሎስን መመለስ በመተረክ እንዲያምኑት አደረጋቸው፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ከተመለሰ በኋላ በልዑል እግዚአብሔር ጥሪ (የሐዋ13፣1-3) በአሕዛብ ሀገር ወንጌልን ለመስበክ ከበርናባስ ጋር ወጡ፡፡ በዚህ ጉዞቸው፡-
በመጀመርያው ጉዞ በጠቅላላ ወደ 2000 ኪ.ሜ የሚደርስ መንገድ በእግር ተጉዟል፡፡ ይህም ጉዞ የተከናወነው በ46 ዓ.ም አካባቢ ነው፡፡ የተሸፈኑትም ሀገሮች ሲሊንውቂያ፣ቆጵሮስ፣ ስልማና፣ ጳፋ፣ጰርጌን፣ገላትያ፣ጵስድያ፣ ኢቆንዮን፣ሊቃኦንያ፣ ልስጥራ፣ ደርቤን፣ጵንፍልያ፣አታልያ እና አንጾኪያ ናቸው፡፡ ሁለተኛው ጉዞ የተከናወ ነው በ50 ዓ.ም ገደማ ነው፡፡ በሁለተኛው ጉዞው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲላስን ይዞ ወደ ኪልቋያ ሶርያ ሲጓዝ በርናባስ ደግሞ ማርቆስን አስከትሎ ወደ ቆጵሮስ ሄደ፡፡ በዚህ ጉዞው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ግሪክ ደርሷል፡፡ የተጓዘባቸውና ያስተማረባቸው ከተሞችም፡-ደርብያ፣ ልስጥራ፣ ፍርግያ፣ ገላትያ፣ ሚስያ፣ ጢሮአዳ፣ ሳሞትራቄ፣ ናፒሊ፣ ፊልጵስዩስ፣ ተሰሎንቄ፣ በርያ፣ አቴና፣ ቆሮን፣ ቶስ፣ አንክራኦስ፣ ኤፌሶን፣ ቂሳርያ፣ ኢየሩሳሌምና አንጾኪያ ናቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የመንፈስ ልጁ ጢሞቴዎስን ያገኘው በዚሁ ጉዞው በልስጥራ ከተማ ነው፡፡
ሦስተኛው ጉዞ በ54ዓ.ም ሲሆን የተሸፈኑትም ሀገሮችም ገላትያ፣ፍርግያ፣ኤፌሶን፣መቄዶንያ፣ፊልጵስዩስ፣ቆሮንቶስ፣ ጢሮአዳ፣አሶን፣ሚሊጢኒን፣ አንጠቀከስዩ፣ትሮጊሊዩም፣መስጡ፣ቆስ፣ሩድ፣ጳጥራ፣ጢሮስ፣ጵቶልማይስ፣ቂሳርያና ኢየሩሳሌም ናቸው፡፡ ከክርስቲያኖች የሰበሰበውን ዕርዳታ ለኢየሩሳሌም ቤተ-ክርስቲያኖች በመያዝ ሦስተኛውን ጉዞ አጠናቅቆ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በኒቆጵልዮን ከተማ ሲያስተምር በ65ዓ.ም ተይዞ ወደ ወኅኒ ገባ፡፡ ለሁለት ዓመት ከስድስት ወር በጨለማ ቤት ታሥሮ ከቆየ በኋላ በ74 ዓመት ዕድሜው በሮም ከተማ በኦስትያ መንገድ አንገቱን ተሠይፎ በ67ዓ.ም ሐምሌ 5 ቀን በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡
በርናባስ ረድእ፡- በርናባስ ማለት የስሙ ትርጉም ወልደ ፍስሐየ ደስታ ልጅ ማለት ነው የተወለደው ቆጵሮስ በሚባል አገር ነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአረገ በኋላ ሀብት ንብረቱን በመሸጥ ለሐዋርያት ሰጥቶአቸዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ ክርስትናው ዓለም ሲጠራ ከሐዋርያት ጋር ያስተዋወቀው እርሱ ነው፡፡ ከቅዱስ ጳውሎስም ጋር በመሆን በልጥራን ያስተምሩ በነበረበት ወቅት አንድ ሕመምተኛ ፈወሱ፡፡ በዚህ ጊዜ የአካባቢው ነዋሪ አማልክት በሰው አምሳል ወደ እኛ ወረዱ ኑ መስዋእት እንሠዋላቸው ብለው ላም ይጎትቱ ጀመር፡፡ እነ ቅዱስ በርናባስም እኛ እንደ እናንተ የምንሞት ሰዎች ነን ተው ብለው ከለከሏቸው የዚያ ሀገር ሰዎችም ስማቸውን ቀይረው ቅዱስ በርናባስን ድያጳውሎስን ሄርሜን ብለው ሰይመዋቸዋል፡፡ ቅዱስ በርናባስም እንዲህ ከሀገር ሀገር እየተዘዋወረ ሲያስተምር ኖሮ ሕዝበክርስቲያኑን ለመጎብኘት ቅዱስ ማርቆስን አስከትሎ ወደ ቆጵሮስ በመመለስ ማስተማር ጀመረ፡፡ ከቆጵሮስ በተጨማሪም ሶርያንና ዲልቅያን ጨምሮ ሲያስተምር አሕዛብ /የማያምኑ/ ጠልተው፤ ተመቅኝተው በድንጋይ በመውገር ነፍሱን ከሥጋው ከለዩ በኋላ ከእሳት ጣሉት፡፡ እሳቱ ግን ሥጋውን ሳያቃጥለው ቅዱስ ማርቆስ አንሥቶ ቀብሮታል፡፡
3.3.14 ወንጌላዊው ማርቆስ (ዮሐንስ)
ኢየሩሳሌም ውስጥ ክርስቲያኖች በቤቷ ለጸሎት ይሰባሰቡ የነበረችው የማርያም ልጅነው፡፡ ሐዋ 12፥12 በርናባስ አጎቱ ነበር፡፡ ከጳውሎስም ጋራ አብሮ አስተምሯል፡፡ በተለይ ግን የጴጥሮስ ተከታይና ተማሪ ስለነበር ልጄ ይለዋል፡፡ 1ኛጴጥ 5፥13 ከጴጥሮስ የሰማውን (የተማረውን) መሰረት በማድረግ በስሙ የሚጠራውን ወንጌል መጻፉን የኢራጶሊስ ጳጳስ ፓፒየስ መስክሯል ማርቆስ ወንጌልን በማስተማር የእስክንድርያን ቤተ-ክርስቲያን መስረቶ በሰማዕትነት አረፈ፡፡ የቬኑስ ነጋዴዎች በዘጠነኛው መቶ ዘመን የቅዱስ ማርቆስን አጽም ወደ ሀገራቸው ወስደው በከተማቸው ውስጥ ባለው በታላቁ የቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል በክብር አስቀምጠውት ከቆየ በኃላ በ1968 ዓም ወደ ግብጽ ተመልሶ አዲስ በተሰራው በቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በክብር አርፏል፡፡
3.3.15 ወንጌላዊው ሉቃስ
አንጾኪያ ውስጥ የግሪክ ወገን ከሆኑ ጣኦት አምላኪዎች ተወለደ፡፡ በጳውሎስ አስተማሪነት ክርስትናን ተቀብሎ የእሱ ደቀ መዝሙር ሆኖ ሲያስተምር ኖረ፡፡ 2ኛ ጢሞ 4፥11 ሐኪምም ነበር፡፡ ቆላ 4፥14 ሠዓሊም እንደነበርና የእመቤታችንን ሥዕል በመጀመሪያ የሳለ እሱ ነው በማለት ብዙዎች ይተርካሉ፡፡በስሙ የሚጠራውን ወንጌልንና የሐዋርያትን ስራ የጻፈ እሱ ነው፡፡ ከመምህሩ ከጳውሎስ እረፍት በኋላ በአካይያ ወንጌልን አስተማረ፡፡ ወንጌልን ሲሰብክ ሲባስ በተባለ ሀገር ውስጥ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡
3.4. ሐዋርያን አበው
3.4.1 የሮም ኤጲስ ቆጶስ ቀሌምንጦስ (88-100)
ቀሌምንጦስ በጥንት ክርስቲያን ዘንድእጅግ የተከበረ አባት ነበር፡፡ የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር እንደ ነበር ይነገርለታል፡፡ ምናልባትም ቅዱስ ጳውሎስ በፊል4÷3 የሥራ ጓደኛዬ ብሎ የጠቀሰውና ፍላቪያን ከሚባለው ከሮም መኳንንት ቤተሰብ ክርስትናን ከተቀበሉት አንዱ ሳይሆን አይቀርም ይባላል፡፡ ቀሌምንጦስ ጠንካራ ክርስቲያን ስለነበረ በ88 ዓ.ም ላይ የሮም ቤተ ክርስቲያን አራተኛ ኤጲስቆጶስ ሆኖ ተሹሟል፡፡ ቅዱስ ቀሌምንጦስ በትራጃን የስደት ዘመን በጥቁር ባሕር ታውሪያን ደሴት [taurian chersonesus] ተግዞ ስለነበር በዚያው ሳለ በአንገቱ ላይ መልሕቅ ታስሮ ወደ ባሕር ውስጥ ተወርውሮ በሰማዕትነት እንደሞተ ይነገራል፡፡
የቀሌምንጦስ ደብዳቤዎች፡- ቅዱስ ቀለሜንጦስ ጽፏቸዋል ተብለው የሚታመኑባቸው ሁለት መልዕክቶች አሉ፡፡
1ኛው መልዕክት፡- በግሪክኛ ቋንቋ ለቆሮንቶስ ቤተ-ክርስቲያን የተጻፈ ነው፡፡ መልዕክቱ የተጻፈበት ዋናው ምክንያት አስቀድሞ በቆሮንቶስ ምዕመናን የነበረውን ብጥብጥና መለያየት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በጻፈላቸው መልዕክቱ 1ቆሮ 1÷10-17፡፡ በሰጣቸው ምክርና ተግሳጽ አብርዶት የነበረው በቀሌምንጦስ ዘመን ተባብሶበት ስለነበርም ዕመኑ በቤተ ክርስቲያን መሪዎችና በካህናቱ ላይተነሳስተው ከሥልጣንም አውርደዋቸው ነበርና ይህንን ብጥብጥና ሁከት ለማብረድ ነበርይህን መልዕክት የተጻፈው፡፡ ምክርና ተግሳጹ ሁሉ ከብሉይ ና ከሐዲስ ኪዳን በተውጣጡ ጥቅሶች የተደገፉ ነበር፡፡ 2ኛው መልዕክት፡- ግን ይዘቱንና የአጻጻፉን ዘይቤ ሲመለከቱት ፈጽሞ መልዕክት አይመስልም፡፡ ይዘቱ በብዙ አቅጣጫ ለምዕመናን በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ የሚሰጥ ስብከት ነው፡፡ ስለ ንስሐ ፣ ስለክርስቲያናዊ ኑሮ ፣ ትንሳኤ ሙታን ስለመኖሩ፣ወዘተ ትክክለኛ ትምህርት ይሰጣል፡፡ ሁለቱንም መልዕክታት አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናትና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ጭምር ከሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትጋር ደምራ ትቀበለዋለች፡፡
3.4.2 የኤፌሶን ኤጲስቆጶስ አግናጥዮስ
የጥንት ቤተክርስቲያን ለቅዱስ አግናጥዮስ “ቴኦፎሮስ” የሚል ቅጽል ሰጥተዋለች፡፡ ትርጉሙም “እግዚአብሔር የተሸከመው” ማለት ነው፡፡ ማቴ. 18÷3 እንደተጻፈው አንድን ህጻን ልጅ በእቅፉ ተሸክሞ “እንደዚህ ሕጻን ካልሆናችሁ መንግስተ ሰማያትን አትወርሱም” ብሏቸዋል፡፡ ያሕጻን አግናጥዮስ ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ስለዚህ ነው አግናጥዮስ “እግዚአብሔር የተሸከመው” የተባለው፡፡
ዳግመኛ አግናጥዮስ የወንጌላዊው የዮሐንስ ተማሪ እንደነበረ ብዙ የጥንት አበው ይናገራሉ፡፡በአንጾኪያም ከቅዱስ ጴጥሮስና ከኤውድዮስ በኋላ ሦስተኛ ኤጲስቆጶስ ነበር፡፡ በ107 ዓ.ም የሮሙ ቄሳር ትራጃን ወደ አንጾኪያ በመጣ ጊዜ በሰማዕትነት መሞቱን በጉጉት የሚመኘው መሆኑን በድፍረት በመግለጡ ቄሳሩ ሮም ተወስዶ ኮሎዚየም በተባለ የትርኢት ቦታ ለአንበሶች እንዲጣል ፈረደበት፡፡ ቅዱስ አግናጥዮስ በአስር ወታደሮች ታጅቦ በባሕርና በየብስ እየተጓዙ በጢሮአዳ በስሚርና በመቄደንያ አድርጎ ወደ ሮም ተጓዘ፡፡ በመንገድ ላይ ሳሉ በጢሮአዳና በስሚርና ከእስረኛጋራ እንዲቆይ ስለተደረገ ለልዩ ልዩ አብያተ ክርስቲያናት ሰባት መልዕክታትን ጻፈ የመጀመሪያዎቹ አራቱ በስሚርና እያለ የጻፈው ሲሆን እነርሱም 1ኛ ለኤፌሶን፣ 2ኛለማግኒስያ፣ 3ኛ ለትራሊያን፣ 4ኛ ለሮም የመጨረሻዎቹ ሦስቱን ግን በጢሮአዳ እያለ ነው የጻፋቸው እነርሱም፡- 5ኛለፊላደልፊያ፣ 6ኛለስሚርና፣ 7ኛ ለኤጲስቆጶስ ፖሊካርፖስ ነው የጻፈው፡፡ በመጨረሻም ታህሳስ 20 ቀን 107 ዓ.ም ለሁለት ትላልቅ አንበሶች ተጥሎ በሰማዕትነት አረፈ ስለዚህም “ምጥው ለአንበሳ” ተብሎ ይጠራል፡፡ለአንበሳ የተሰጠ ማለት ነው፡፡
3.4.3 የእስሚርናኤጲስ ቆጶስፖ ፖሊካርፖስ (አቡሊ ካሪዮስ)
ቅዱስ ፖሊካርፖስ ከሐዋርያት በኋላ ከተነሱት አባቶች እጅግ የታወቀ አባት ነው፡፡ የተወለደው በ69 ዓ.ም ነው፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ በኤፊሶን ከወንጌላዊው ዮሐንስ ጋራ የኖረና ተማሪ ብቻ ሳይሆን የቅርብ ወዳጁም እንደነበረ ይነገራል፡፡ ቅዱስ ፖሊካርፖስ እጅግ የተማረ ብቻ ሳይሆን በጣምም መንፈሳዊ ሰው ስለነበር፡፡ መምህሩ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ ፖሊካርፖስን የስሚርና (የሰርምኔስ) ኤጲስ ቆጰስ አድርጎ ሾሞታል፡፡ በዚያን ዘመን አይሁድ በሰርምኔስ በብዛት ስለነበ ሩበአይሁድ አነሳሽነት ሮማውያን በክርስቲያኖች ላይ ታላቅ ስደት አስነስተው ነበር፡፡ ፖሊካርፖስም ሮምን በጎበኘ በአመቱ በ155ዓ.ም ተይዞ ስቃይ ወደ ሚቀበልበት ቦታ ተወሰደ ስታቲያስኳ ድራቱስ የተባለው ሮማዊ ገዥ ምህረት ይደረግለት ዘንድ ክርስቶስን እንዲክድና እንዲሳደብ ደጋግሞ በጠየቀው ጊዜ በመጨረሻ “ክርስቶስን 80ዓመት ሙሉ ሳገለግለው አንድ ቀን እንኳ ክፉ ነገር ያላደረገብኝንጌ ታዬንና መድኃኒቴን ፈጽሞ አልክደውም” ሲል መለሰለት፡፡ ቀጥሎ ገዢው “ለወጣትነት እድሜህ አስብለት ቄሳርን ጌታ ብለህ ተቀበልና ለምስሉም ዕጣን አጥንናእኔም ከዚህ ስቃይ አድንሃለሁ በእሳት እኮ ነው የምትቃጠለው” ብሎ ሊያስፈራራው ቢሞክር “አሁን ነድዶ በኋላ የሚጠፋው ንእሳት ነው የምትለው ለዘለዓለም የማይጠፋውን ለኃጥያተኞች የተዘጋጀውን እሳት ማሰብ አለብህ” በማለት ወደ ሚሰቃይበት ቦታ ቀጥ ብሎ ሄደ በዚህ ጊዜ ከሰማይ “ፖሊካርፕ!!! አይዞህ በርታ እንደዚህ ወንድ ሁን!” የሚል ድምጽ በሱ ብቻ ሳይሆን እዚያ በተሰበሰበው ሕዝብ ሁሉ ጆሮ ተሰማ፡፡ እሳቱ ተያይዞ ሰውነቱ ሲቃጠል ከእሳቱ ይወጣ የነበረው ሽታ ዕጣን ዕጣን የሚል ነበር፡፡ ምዕመናን አጥንቶቹን ሰብስበው በክብር በቤተ-ክርስቲያን አስቀመጡት፡፡
